በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስር የሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ንብረቶች በግልጽ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ማስታወቂያ

በአፈ/ከሳሾች እነ ወ/ሮ ፋና ጋብሶ 245 ሰዎች እና በአፈ/ተከሳሽ የኳድራንት አፓረል ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ የአፈ/ተከሳሽ ንብረቶች የሆኑት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ገምቶ በላከዉ ግምት መሰረት በመነሻ ዋጋ 38,336,889.13 ብር (ሰላሳ ስምንት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰላሳ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር ከ13/100 ሳንቲም) በማድረግ ፍ/ቤቱ በግልጽ ጨረታ እንዲሸጥ የወሰነ ስለሆነ ጨረታዉን መጫረት የሚፈልጉ ተጫራጮች ከዚህ ያለዉን ዝርዝር መረጃ በመመልከት መጫረት እንዲችሉ በጋዜጣችሁ ታትሞ እንዲወጣ ፍቤቱ አዟል።

በመሆኑም፡-

  • በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ለጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን 1/4ኛ በሞዴል 85 በሀዋሳ ከተማ የመጀ/ደረጃ ፍ/ቤት ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ በአካል ቀርባችሁ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ማስታወቂያው ከቀን 19/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 03/11/2018 ዓ.ም ድረስ በአየር ላይ ውሎ ጨረታው በቀን 06/11/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5፡00 ሰዓት ድረስ ይካሔዳል።
  • ዋና ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች ጨረታውን መጫረት ትችላላችሁ።
  • ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ሙሉ የጨረታ ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ገቢ ካላደረገ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ በድጋሚ የጨረታ ማስታወቂያ እንዲወጣ ይታዘዛል።
  • በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ እንዲደረግ ይታዘዛል።
  • ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ያሸነፈበትን ሙሉ የጨረታ ዋጋ አጠቃሎ ከከፈለበት ጊዜ ጀምሮ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ በጨረታ ያሸነፈበትን ዕቃዎች እንዲረከብ ይታዘዛል።
  • ጨረታው የሚከናወነው በሀዋሳ ኢንዱስትሪያ ፓርክ ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስር የሀዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-13
  • Publishing entity: Hawassa City First Instance Court
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 10, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders