የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የባለ 10 ቶን ሃፍ ክሬን እና 40 ቶን ሎውቤድ ኪራይ አገልግሎት ግዥ፣ አንድ ሃይድሮሊክ ክሬን ወይም አንድ ባለ 130 ቶን ተንቀሳቃሽ ክሬን እና 100 ቶን ለውቤድ ኪራይ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረት ቁጥር EEP/TBP/01/2019

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  • ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።
  • ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት ህንፃ ቁጥር- 11ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ወይም በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በEEP Transmission Substation Construction Account No.1000252665203 ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-19 ትራንስሚሽን ቢዝነስ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 114 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
  • ከትራንስሚሽን ቢዝነስ ግዥ ቢሮ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  • ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን የኪራይ አገልግሎት ግዥ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/14/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የኪራይ አገልግሎት ግዥ መወዳደር ይችላሉ።

የአገልግሎት ግዥ ዓይነት

ሎት

የጨረታ ማስከበሪያ

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት

የባለ 10 ቶን ሃፍ ክሬን እና 40 ቶን ሎውቤድ ኪራይ አገልግሎት ግዥ

1

80,000.00 (ሰማንያ ሺህ ብር)

ሀምሌ 15 ቀን ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት  

 

ሀምሌ 15 ቀን ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት  

 

አንድ ሃይድሮሊክ ክሬን ወይም አንድ ባለ 130 ቶን ተንቀሳቃሽ ክሬን እና100 ቶን ለውቤድ ኪራይ አገልግሎት ግዥ

2

90,000.00 (ዘጠና ሺህ ብር)

  • ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116732205 መደወል ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-22
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-22 14:15
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Power
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published: Jul 11, 2026
  • Posted at: 2026-07-11T08:00:25.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders