በጉለሌ ክ/ከ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ አገልግሎቶችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/ 2019 ዓ/ም

በጉለሌ ክ/ከ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ አገልግሎቶችን ለ2019 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡- የመኪኖች ኪራይ
  • ሎት 2፡- የድንኳን ኪራይ
  • ሎት 3፡- ህትመት አገልግሎት
  • ሎት 4፡- የሞንታርቦና የመድረክ እስቴጅ ኪራይ
  • ሎት 5፡-፡-የኮምፒውተር ፣ ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና

1. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን ፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው እቃ ወይም አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልጽ ለይተው መጻፍ አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ድረ ገጽ (ዌብ ሳይት) ላይ በዘርፉ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ላይ ወይም አገልግሎቶች ሳምፕል ወይም ናሙና ለመስሪያ ቤቱ በማቅረብ የጥራትና የቴክኒክ ኮሚቴዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመግማሉ፡፡

6. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ የቀረበውን እስፔሲፊኬሽን በመሰረዝ በመደለዝ ማሻሻያ ማድረግና መለወጥ አይችሉም።

7. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጃችሁ ተጫራቾች ካደራጃችሁ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው። ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያከተተ ተደርጎ ይወሰዳል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ ለሎት 1፡- 20,000 ለሎት2፡ 20,000፤ ለሎት3፡ - 20,000 ፤ ለሎት4፡- 20,000 ለሎት 5፡ 20,000 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ የጠቅላላ ዋጋ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።

10. የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኤንቨሎፕ ታሽገው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ፊርማቸውንና ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይ በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

11. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል በስራ ሰዓት ጉለሌ ክፍለ ከተማ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15 የጉ/ክ/ከ/አ/ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች /ፑል/ የአስ/ፋይ/ፅ/ቤት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡

12. የካፒታል መጠናቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ የሆነ ተጫራቾች ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

13. የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው የስራ ቀን ከሆነ በ10 ተከታታይ ቀናቶች በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በመግዛት መወዳዳር የምትችሉ መሆንን እየገለጽን ጨረታው አየር ላይ በዋለ 11ኛው ቀን ባለው የስራ ቀን 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 በጉ/ክ/ከ/የዲ/ግ/ስ/ፑል/የአስ/ፋይ/ፅ/ቤት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

15. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናሉ።

16. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

17. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።ይህ ባይሆን ከጨረታ ይሰረዛሉ።

18. ተጫራቾች በንግድ ፈቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው።የተጫራቾች ማህተም እና የንግድ ፍቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኛቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል።

19. በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል።

20. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ባይሆን ግን በጨረታ የስያዙት /ሲፒኦ/ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።

21. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ እንዲሁም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የእቃ ብዛት ቀንሶ ወይም ጨምሮ ከአሸነፈው ድርጅት የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

22. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ የተዘረዘሩት እቃዎች ላይ በቀረበው እስፔሲፊኬሽን መሰረት ናሙና ውይም ሳምፕል ማስገባት ይኖርበታል።

ማሣሰቢያ

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገዎ በስልክ ቁጥር 011-8 12 10 96 ይደውሉ።
የጉለሌ ክ/ከ/ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን ባለው የስራ ቀን 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-24 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን ባለው የስራ ቀን 4:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Design and Building Works Pool Administration & Finance Office
  • Buyer address: አዲሱ ገበያ ከኖክ ማደያ ጀርባ
  • Bid bond: 20,000.00 ብር በየሎቱ
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published: Jul 12, 2026
  • Posted at: 2026-07-13T07:12:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders