አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. ለፋብሪካ እና ተመሳሳይ አገልግሎት የሚዉል መጋዘኖች በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል

Description

የመጋዘን ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

1. አቢሲንያ ባንክ አ.ማ.ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ላይ የተገለጹትን በዕዳ ማካካሻነት የወረሰውን በከተማ ደጋጋ ወረዳ ዉስጥ የሚገኘውን ለፋብሪካ እና ተመሳሳይ አገልግሎት የሚዉል መጋዘኖች በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።

.

የንብረቱ ዓይነት

የሚከራየዉ ንብረት የሚገኝበት አድራሻ

ጠቅላላ ስፋት በካሬ ሜትር

የአንዱ ካሬ ሜትር የጨረታ መነሻ ዋጋ

1

የፋብሪካ መጋዘኖች እና G+2 ፎቅ ቢሮ አገግሎት የሚዉል

አዳማ ከተማ ደጋጋ ወረዳ

ሙሉ ግቢ ጠቅላላ ስፋቱ 2,499.75 ካሬ ሜትር ሲሆን የሚከራየው መጋዘን እና ቢሮ 1,916.89 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ የፋብሪካ መጋዘን እና G+2 ፎቅ የሆነ ቢሮ አገልግሎት የሚዉል ሕንጻ ነው::

  • ተጫራቾች የየራሳቸዉን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ::
  • የሚቀርበዉ ዋጋ ..ታክስ ጨምሮ ወይም ሳይጨምር መሆኑ ገለ አለበት::

ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በካሬ ሜትር እንዲሆን እናሳስባለን።

2. ተጫራቾቾ ስኪራይ ዋጋ ማቅረቢያ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ፍራንኮ ሳራ ሞል በሚገኘዉ የአቢሲንያ አዳማ ዲሰትሪክት ሁለተኛ ፎቅ የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ብር 100.00 (ብር አንድ መቶ ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. የሚከራዩትን ንብረቶች ለተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቀጠሮ በማስያዝ በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚከራዩበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ከጨረታ ሰነዱ ላይ መገስጽ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የሚከራዩበትን ዋጋ (ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ) እና የሚከራዩትን ንብረት ለምን አገልግሎት እንደሚያውሉት በትክክል ጠቅሰው በታሸገ ኢንቨሎፕ እሰከ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ፍራንኮ ሳራ ሞል በሚገኘዉ የአቢሲንያ አዳማ ዲሰትሪክት ሁለተኛ ፎቅ ከሚገኘዉ የባንኩ የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታጡ ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ፍራንኮ ሳራ ሞል በሚገኘዉ የአቢሲንያ አዳማ ዲስትሪክት ሁለተኛ ፎቅ የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።

7. ተከራይ ለሚከራዩት ንግድ ቤት በጨረታ ያሸነፉበት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ይከፍላሉ።

8. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ንብረት ብር 10,000.00 (ብር አስር ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች የጨረታ ውጤቱ በተገለጸ በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ የኪራይ ውል ከባንኩ ጋር መፈጸም ይኖርበታል።

10. የጨረታው አሸናፊ በተራ ቁጥር 9 መሠረት በተጠቀሰው ቀን ቀርቦ ውል ካልፈጸመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

11. ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እሰከ 10 ድረስ ከተዘረዘሩት ነጥቦች አንዱን አለመፈጽም ከጨረታ ለመሰረዝ ምክንያት ይሆናል።

12. ባንኩ ስለኪራዩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

13. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022 212 0441 እና 0911 176 493 ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ።

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-07-15
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-15 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jul 12, 2026
  • Posted at: 2026-07-13T10:53:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders