የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኝ ለጋራዥ አገልግሎት እስከነ ቢሮው የሚውል ቦታን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

የጋራዥ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር-EMC/OT/GARAGE RENT/01/2019

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኝ ለጋራዥ አገልግሎት እስከነቢሮው የሚውል ቦታን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

ሎት

የዕቃው ዓይነት

ብዛት

ጠቅላላ ስፋት

የጨረታው መዝጊያ

የጨረታው መክፈቻ

ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ

ቀን

ሰዓት

ቀን

ሰዓት

 

ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ

1

1093.65m2

 

29/11/2018 ዓ.ም.

4፡00 ጠዋት

29/11/2018 ዓ.ም

4፡30 ጠዋት

አ.አ ዋናው መስሪያ ቤት

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች (መመሪያዎች)፡-

1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የኪራይ በዘርፉ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ  ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value added tax) ተመዝጋቢ መሆናቸውን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)፣ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚሰጥ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው አድራሻ በቢሮ ቁጥር ብሎክ በግንባር በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሶፍት ኮፒ(soft copy) መውሰድ ይችላሉ።

2. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለኪራይ የተዘጋጀውን ጋራዥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታውን ለመክፈት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ጋራዡ በሚገኙበት ቦታዎች በአካል በመገኘት ኮርፖሬሽኑ በሚመድበው ሰራተኛ አስጎብኚነት መመልከት ይችላል።

3. ተጫራቾች ለሚከራየው ጋራዥ የሰጡትን ጠቅላላ ዋጋ ብር 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ከሰነዳቸው ጋር የማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል። አሸናፊ ለሆኑትና ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ህጋዊ ባንክ ከሆነ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ሊታሰብላቸው ይችላል ወይም ለተሸነፉት ተመላሽ ይደረጋል።

4. የጨረታ አሸናፊው ጋራዥ ኪራይ ቅድሚያ የሶስት ወራት የሚከፍሉ ይሆናል።

5. ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በላዩ ላይ ድርጅቶች ከሆኑ ማህተም ያረፈበት፣ የግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ ሶስት ፊርማ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው።

7. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንን በተመለከተ ከላይ በሰንጠረዥ ዋናው መ/ቤት በተገለጸው ቀን እና ሰዓት መሰረት ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 በዋናው መ/ቤት ይከፈታል

8. ተጫራቾች ለሚከራዩት ጋራዥ ስፋት ካሬ ሜትር ዋጋ በቁጥርና በፊደል ስርዝ ድልዝ የሌለበት በግልጽ ሞልተው በታሸገው ኤንቬሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ የሚኖርባቸው ሲሆን ገዥ የሚሆነው የነጠላ ዋጋው ይሆናል።

9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 09 11 62 22 63 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

10. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ

+251-09 11 62 22 63

የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Publishing entity: Ethiopian Mineral Corporation (EMC)
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jul 19, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders