ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. አዲስ ላስገነባው 3B+G+25 ሕንጻ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች (imported Office Furniture) ማለትም፡- የቢሮ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ የእንግዳ ወንበሮች፣ የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮችና ጠረጴዛዎች እና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ ኢማ
እቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ አዲስ ላስገነባው 3B+G+25 ሕንጻ የተለያዩየቢሮ ዕቃዎች (imported Office Furniture) ማለትም፡- የቢሮ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ የእንግዳ ወንበሮች፣ የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮችና ጠረጴዛዎች እና የመሳሰሉትን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው፡-
1.የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ብቁ ልምድ ያላቸው።
2. ተጫራቾች ስለ ጨረታው የሚገልፀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋናው መ/ቤት ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ (22ኛ ፎቅ) በመምጣት የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና የሚጫረቱበትን ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከሚጫረቱበት ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የመጫረቻ ሰነድ እና ዋጋ በኤንቬሎፕ በማሸግ እስከ ከሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የኩባንያውዋና መ/ቤት 22ኛ ፎቅ ላይ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በዕለቱ ከሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው ዋና መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
6. ኩባንያው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ናይል ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ዋና መ/ቤት (ብሔራዊ ቴአትር ጀርባ) ሀብት ሥራ አመራር መምሪያ (22ኛ ፎቅ)
የስልክ ቁጥር፡- 09 11 48 08 45/09 11 43 02 92
አዲስ አበባ።
Tender details
- Deadline: 2026-07-30
- Publishing entity: Nile Insurance Company S.C.
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
- Published: Jul 12, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.