የጎማ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጎማ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት የተለያዩ 1. የጽህፈት መሣሪያ (አላቂ) ዕቃዎችን 2. የቢሮ ውስጥ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች፡ 3. የፅዳት ዕቃዎችን፣ 4. የግንባታ መሣሪያዎችን፡ 5. የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን፣ 6. የደንብ ልብስ፤ 7. የህትመት ስራ፤ 8. የተለያዩ የመኪና እና የሞተር ሣይክል ጎማዎችን ግዥ፣ 9.የተለያዩ መኪናዎች እና ሞተር ሣይክሎች ጥገና፣ 10.የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣ 11. የሞተር ሳይክልና የባለ ሦስት እግር ባጃጅ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራች ድርጅቶች፡-
- በሥራው ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም ግብር ከፍለው ፍቃዳቸውን ያሳደሱ
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 0.5-1% CPO ማስያዝ የሚችሉ።
- አሸናፊ ድርጅቶች ማሸነፋቸው በተነገራቸው በ5(አምስት) ቀን ውስጥ ቀርበው ውል መፈፀም የሚችሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ናሙና ማቅረብ የሚችሉ።
- የሚቀርበው ዕቃ በኢትዮጵያ ደረጃ መዳቢዎች የተሰጠ የጥራት ማረጋገጫ ሊኖረው ይገባል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- አሸናፊ ድርጅቶች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ዋጋ እና መረጃዎችን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒውን ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተወዳዳሪ ድርጅቶች ከሀገር ውስጥ ገቢ ፅ/ቤት የአመቱን ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት በመ/ቤቱ ቀርበው የማይመለስ ብር 300(ሶስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
- አሸናፊ ተጫራቾች በተመረጠው ናሙና መሠረት በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃዎች የመ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችሉ።
- ጨረታው በ23/11/2018 ዓ/ም በ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ24/11/2018 ዓ/ም በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሣሰቢያ- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 047 221 1231
በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/በጅማ ዞን የጎማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-30
- Publishing entity: Jimma Zone Goma Woreda Finance Office
- Bid bond: ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ 0.5-1%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jul 13, 2026
Categories
StationeryOffice Supplies and ServicesOffice Machines and AccessoriesComputer and AccessoriesIT and TelecomEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsPrinting and PublishingSpare Parts and Car Decoration MaterialsTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseOthersMaintenance and RepairVehicle (garage service)House FurnitureFurniture and FurnishingOffice FurnitureCleaning and Janitorial Equipment and ServiceBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksConstruction Machinery and EquipmentTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsTextile, Garments and UniformsAmharic2merkatoJimma Zone Goma Woreda Finance OfficeOromia
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.