ብርሃን ባንክ በ2019 በጀት ዓመት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ ጠረጴዛዎች፣ የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የተለያዮ የቢሮ ፈርኒቸሮች ግዢ ጨረታ

አገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ

1. ብርሃን ባንክ በ2019 በጀት ዓመት የሚውሉ ከዚህ በታች በሰንጠርዥ የተዘረዘሩትን የተለያዮ የቢሮ ፈርኒቸሮች ግዥ ለማከናውን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም

ምድብ ቁጥር

ዓይነት

ብዛት

 

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ቁጥር

I

የተለያዩ የቢሮ ጠረጴዛዎች

በብዛት

ዝርዝር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን በጨረታ ሰነዱ ላይ ተጠቅሷል።

22/11/2018 . 4:00 ሰዓት

//ግጨ /2026/27/04

II

የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች

በብዛት

22/11/2018 . 4:00 ሰዓት

//ግጨ//2026/27/05

 

2. ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የምስክር ወረቀት እና የታክስ ከፋይነት የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች ለእያንደንዱ ምድብ የማይመለስ ብር 345.00 (ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር) በማንኛዉም የብርሃን ባንክ ኢማ ቅርንጫፍ ክፍያ ፈፅመዉ ደረሰኙን በማቅረብ፣ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ከባንኩ የሰፕላይ ቼን እና ዉል አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ለጨረታዉ የተዘጋጀዉን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የቴክኒክ ሰነድ እና የዋጋ ስነድ አንድ በዋና እና አንድ በኮፒ በተለያዮ ፓስታ ማቅረብ እንዲሁም ናሙና ማሳየት አለባቸው።

5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ከላይ በሰንጠረዥ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ የሰፕላይ ቼን እና ዉል አስተዳደር መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማሰገባት አለባቸው።

6. በምድብ 1 ላይ የተጠቀሰዉ የቢሮ ጠረጴዛ ጨረታ በ22/11/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በዛዉ ቀን በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን በምድብ 2 ላይ የተቀመጠዉ የቢሮ ወንበሮች ጨረታ ደግሞ በ22/11/2018 ዓ.ም በ4፡00 ተዘግቶ በዛዉ ቀን በ5፡00 ላይ ይከፈታል።

7. ጨረታው ከላይ በሰንጠረዥ በእያዳንዱ ምድብ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኋላ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ከሚገኝበት ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ከሚገኘዉ ወመሳድኮ ህንፃ 2ተኛ ፎቅ የሰፕላይ ቼን እና ዉል አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ይከፈታል።

8. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።

ብርሃን ባንክ አ.ማ.

የሰፕላይ ቼን እና ዉል አስተዳደር መምሪያ

ስልክ ቁጥር 011 663 2097/011 650 7422


Tender details

  • Deadline: 2026-07-29
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-29 11:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ሰዓት ይለያያል
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Berhan Bank S.C.
  • Bid document price: 345.00 ብር ለእያንደንዱ ምድብ
  • Published: Jul 12, 2026
  • Posted at: 2026-07-13T11:22:57.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders