ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ. የተለያዩ የፎርድ መለዋወጫ ዕቃዎች መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተዘረዘሩት የተለያዩ የፎርድ መለዋወጫ ዕቃዎች አጠቃላይ መመሪያዎች እና ግዴታዎች፦

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ደንበኞች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 20 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገኤንቬሎፕ በማቅረብ በጨረታ ሰነድ ቅጽ ላይ በመሙላትና ለጨረታ ማስከበሪያም ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) በ ሲፒኦ ብቻ በማስያዝ በድርጅቱ የፎርድ መለዋወጫ ዕቃዎች ዲቪዥን ክፍል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  3. በዚህ የግዢ ጨረታ የሚቀርቡ ሰነዶች በሙሉ በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ መጻፍ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ለመግዛት የወሰኑበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ለእያንዳንዱ መለዋወጫ ዕቃ መለያ ቁጥር በተናጥል መጥቀስ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚፈልጉትን የሚለዋወጫ አይነት በመለየት በጥቅል ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ የፎርድ መለዋወጫ ዕቃዎች ዲቪዥን ገንዘብ ተቀባዮች ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  7. ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ዘግይተው የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
  8. ጨረታው የጨረታ ሰነዱን ማስገቢያ ጊዜ ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የሰራተኞች ክበብ ውስጥ ይከፈታል።
  9. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በማስታወቂያ ከተገለጸ ቀን አንስቶ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ ዕሴት ታክስን ጨምሮ ክፍያ መፈጸም ይኖርባቸዋል።
  10. በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ፈጽመው ያሸነፉበትን ዕቃዎች የማያነሱ ከሆነ በእቃዎቹ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  11. የጨረታ ተሸናፊዎች ዝርዝር በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 442 1133 / 09 44 06 80 06

ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Publishing entity: Ries Engineering S.C.
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 1000.00 ብር
  • Published: Jul 14, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders