ፀደይ ባንክ አ.ማ. በብዛት 80,000 QR Stand በሶስት የተለያዩ አይነቶች ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ 0021/2018
ፀደይ ባንክ አ.ማ በብዛት 80,000 QR Stand በሶስት የተለያዩ አይነቶች ከስር በሰንጠረዡ በተዘረዘረው ብዛት ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
የዕቃው አይነት |
|
ብዛት |
|
QR Stand |
አይነት አንድ |
35,000 |
|
አይነት ሁለት |
10,000 |
|
|
አይነት ሶስት |
35,000 |
ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት ነጋዴ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።
1. የ2018 ዓ ም የታደስ ንግድ ፈቃድ # የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት # በጨረታ ለመካፈል ለመሳተፍ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ክሊራንስ ጊዜው ያላለፈበት:: ቴክኒካል ዶክመንትና የሚያቀርቡበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% ወይም የአጠቃላይ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ90 ቀን በፀደይ ባንክ አማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል:: ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።
3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ አምስት መቶ ብር /500.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው እስከሚዘጋበት ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: ጨረታው በተዘጋበት ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
5. የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።
6. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ በሚገኘው የፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት
ስልክ ቁጥር፦ 0115581658
ፀደይ ባንክ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-07-29
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-29 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
- Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: Jul 15, 2026
- Posted at: 2026-07-15T08:49:54.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.