ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ለምርት ሂደቱ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎች፣ ኬሚካሎች፣ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች፣ መለዋወጫዎች እና ሌሎች የአቅርቦት እቃዎችን በተሻለ ጥራት፣ በተወዳዳሪ ዋጋ እና በተረጋጋ አቅርቦት ለማቅረብ የሚችሉ ብቁ አቅራቢዎችን ለመለየት የቅድመ ብቃት ማረጋገጫ ጨረታ ይጋብዛል
Description
የቅድመ ብቃት ማረጋገጫ (Pre-Qualification) ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ለምርት ሂደቱ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎች፣ ኬሚካሎች፣ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች፣ መለዋወጫዎች እና ሌሎች የአቅርቦት እቃዎችን በተሻለ ጥራት፣ በተወዳዳሪ ዋጋ እና በተረጋጋ አቅርቦት ለማቅረብ የሚችሉ ብቁ አቅራቢዎችን ለመለየት የቅድመ ብቃት ማረጋገጫ ጨረታ ይጋብዛል።
በመሆኑም ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ አምራቾች፣ አስመጪዎች፣ አከፋፋዮች እና በተመለከተው ዘርፍ ብቃትና ልምድ ያላቸው ድርጅቶች በዚህ የቅድመ ብቃት ሂደት እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
አመልካቾች ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች
1. የህጋዊ ብቃት ማረጋገጫ
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት
- TIN ሰርተፍኬት
- VAT ምዝገባ ማስረጃ (ተገቢ ከሆነ)
- የግብር ክሊራንስ
2. የቴክኒክ ብቃትና የጥራት ማረጋገጫየሚቀርበው ዕቃ ዝርዝርና ቴክኒክ መግለጫ
- የአምራች መረጃ ወይም የተፈቀደ አቅራቢነት ማስረጃ
- የጥራት ማረጋገጫ
- Certificate of Analysis (CoA)SDS/MSDS (ለሚመለከታቸው እቃዎች)
3. የልምድና የአቅርቦት አቅም
- ተመሳሳይ ዕቃ የማቅረብ ልምድ
- የቀድሞ የአቅርቦት ውል ወይም የደንበኛ ማጣቀሻ
- የማከማቻና የማጓጓዣ አቅም
- የአቅርቦት ጊዜ ማረጋገጫ
4. የአስመጪነትና የአቅራቢነት ማስረጃ
- የአስመጪነት ፈቃድ
- ከውጭ አምራች የተሰጠ የውክልና/ አቅራቢነት ማስረጃ
- የአምራች ማረጋገጫ ደብዳቤ (ካለ)
5. የፋይናንስ አቅም ማረጋገጫ
- የፋይናንስ አቅም ማስረጃ
- ተመሳሳይ ግዥ ለመፈጸም የሚያስችል አቅም
- ተገቢ የፋይናንስ መረጃ
6. የደህንነትና ህግ ተገዢነት
- የደህንነት መረጃዎች
- የማከማቻና የማጓጓዣ መመሪያዎች
- በህግ የሚጠየቁ ተጨማሪ ፈቃዶች
- ሌሎች በግዥ አካሉ የሚጠየቁ ሰነዶች
- የግምገማ ሂደት የሚቀርቡ ሰነዶች በህጋዊ ብቃት፣ በቴክኒከ አቅም፣ በጥራት፣ በልምድ፣ በፋይናንስ አቅም እና በአቅርቦት ብቃት መሰረት ይገመገማሉ።
ተጫራቾች የቅድመ ብቃት ሰነዶቻቸውን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው። በቀን ከ07/11/2018 እስከ 21/11/2018 ዓ.ም በተከታታይ 15 ቀናት ዉስጥ ማስገባት አለባቸው። የመጨረሻ ማቅረቢያ ቀን፡ 22/11/2018
የማቅረቢያ ቦታ፡- ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
ማሳሰቢያ፡- ይህ ማስታወቂያ ለቅድመ ብቃት ምዝገባ ብቻ ሲሆን የዉል ሽልማት አይደለም፡፡ ድርጅቱ ያቀረበው ሰነዶችን የማረጋገጥ፤ ተጨማሪ መረጃ የመጠየቅ፤ እንዲሁም ማንኛውንም ወይም ሁሉንም ማመልከቻዎች ያለምንም ግዴታ የመቀበል ወይም ያለመቀበል መብት አለው።
መከላኪያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩብ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዶኩመንቱ የሚገበዉ በሃርድ ኮፒ ወይም በኢሜይል dhugumafita@gmail.com መሆኑን በአክብሮት እየገለፅን።
በተጨማሪ በስልክ ቁጥር 09 99 15 08 75 / 09 69 39 19 69 ወይም +251-11-219-0042 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል።
መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ
Tender details
- Deadline: 2026-07-29
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-07-29 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Homicho Ammunition Engineering Industry
- Published: Jul 15, 2026
- Posted at: 2026-07-15T08:55:08.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.