የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (Ethiopian Veterinary Association-EVA) የተለያዩ የእንስሳት መድኃኒቶች እና የመገልገያ መሣሪያዎችን በአስቸኳይ ግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሣሪያዎች
ለመግዛት በድጋሜ የወጣ አስቸኳይ ግልጽ የጨረታ
ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ EVA/NCB /Drugs 03/2026
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (Ethiopian Veterinary Association-EVA)
- የተለያዩ የእንስሳት መድኃኒቶች እና
- የመገልገያ መሣሪያዎችን በአስቸኳይ ግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከታች የተቀመጡ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎችና አከፋፋዮች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ማኅበሩ ይጋብዛል።
1. መቅረብ የሚገባቸው ሕጋዊ ማስረጃዎች
1.1. የታደሰ የንግድ ፈቃድና የ2018 ዓ.ም ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣
1.2. የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሣሪያዎች ለማስመጣት ወይም በጅምላ ለማከፋፈል በሚመለከተው የመንግሥት ተቆጣጣሪ አካል የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት የተሰጠውና ለ2018 የግብር ዘመን የታደሰ፣
13. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ምስክር ወረቀት፣
1.4. በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባቸው የሚያሳይ የምስክር ወረቀት፣
2. የጨረታ ሰነድ ግዥ ሂደት
2.1. ፍላጎት ያላቸው እና ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማኅበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 303/306 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርቦ በነጻ ማግኘት ይችላሉ።
2.2. ሰነዱን መውሰድ የሚቻለው ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2:30 እስከ 6:30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 እስከ 10:30 ባሉት የሥራ ሰዓታት ውስጥ ነው፦
2.3. ተጫራቾች የእያንዳንዱን መድኃኒት ወይም መገልገያ መሣሪያ ዋጋ በራሳቸውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰንድ (Proforma form) በግልጽ ሞልተውና የድርጅቱን ማኅተም አድርገውበት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ማኅበሩ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
2.4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፣ ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ፣ ቼክ ወይም CPO፧አሸናፊ ድርጅት ከተለየ በኋላ ወዲያኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
2.5. ጨረታው በ7ኛው ቀን በ11፡30 ላይ ይዘጋል፣ በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
2.6. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦
በስልክ ቁጥር:- +251-115-525-020; 091189490209;0904327608; 0911185503
አድራሻ፦ ከእንግሊዝ ኢምባሲ (British Embassy) ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ 600 ሜትር
ገባ ብሎ ይመናሹ ሕንጻ ፊት ለፊት።
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-21
- Publishing entity: Ethiopian Veterinary Association
- Bid bond: 2%
- Published: Jul 15, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.