ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በባህር ዳር ከተማ ለሚገኘው የ "OncoE6 Cenical Test” ማምረቻ ፋብሪካ የ ISO 13485:2016 ዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ ዙር የምስክር ወረቀት (Initial Certification Audit) ለመስጠት የሚያስችል ብቃትና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የብቃት ማረጋገጫ ሰጪ አካላት (Certification Bodies) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈ
Description
የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡ Med×/TND/ISO13485/2018-002
የፕሮጀክቱ ስም፡ የISO 13485:2016 የህክምና መሳሪያዎች የጥራት አስተዳደር ስርዓት ሰርተፊኬሽን አገልግሎት ግዥ
ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በባህር ዳር ከተማ ለሚገኘው የ "OncoE6 Cenical Test” ማምረቻ ፋብሪካ የ ISO 13485:2016 ዓለም አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያ ዙር የምስክር ወረቀት (Initial Certification Audit) ለመስጠት የሚያስችል ብቃትና ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የብቃት ማረጋገጫ ሰጪ አካላት (Certification Bodies) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
1. ዋና ዋና የስራ ዝርዝሮች (Scope of the Service)
- የኦዲት ደረጃዎች፡ ደረጃ 1 እና ደረጃ 2 ኦዲትን በሰነድ ምርመራ እና በባህር ዳር ማምረቻ ጣቢያ በአካል በመገኘት ማከናወን፤
- የኦዲት ወሰን፡ የህክምና መሳሪያዎች መገጣጠም፣ ማሸግ፣ ሌብል ማድረግና የጥራት ቁጥጥር ሂደቶችን ሙሉ በሙሉ መገምገም፤
- የምስክር ወረቀት፡ ለ3 ዓመት የሚያገለግል እውቅና ያለው የISO 13485:2016 ሰርተፊኬት መስጠት እና ዓመታዊ የክትተል ኦዲቶችን ማካሄድ ናቸው።
2. የተጫራቾች መወዳደሪያ መመዘኛ መስፈርቶች
- የመጀመሪያ ህጋዊነት (የማለፊያ መስፈርት)፡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣ የTin እና Vat ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ እና የISO 13485 ወሰንን ለመመርመር የሚያስችል የእውቅና ማረጋገጫ ያለው እና ማቅረብ የሚችል፤
- የቴክኒክ ብቃት(ክብደት 30%(የማለፊያ ነጥብ 30)፡ በህክምና መሳሪያዎች ኦዲት ላይ ያለው የሥራ ልምድ (15 ነጥብ)፤ የኦዲት ጊዜ ሰሌዳና አሰራር ዘዴ(15 ነጥብ) ይሆናል።
- የፋይናንስ ብቃት (ክብደት 70%) ፡ የሶስት አመቱን ሙሉ ሰርተፊኬሽን ኡደት ያካተተ ቋሚ ዋጋ በኢትዮጵያ ብር ማቅረብ አለባቸው።
3. የጨረታ ሰነድ አቀራረብና መመሪያ
- ሰነድ መግዣና ማስገቢያ: ሬስ ኢንጅነሪንግ ህንፃ 2ኛ ፎቅ በሚገኘው ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ቢሮ ፋይናንስ ክፍል በመምጣት ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል በተለያዩ በታሸጉ ኢንቨሎፖች በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት እና እንዲሁም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ 2000.00 ብር/ ሁለት ሺህ ብር/ በአካል በመቅረብ መመዝገብ እና መክፈል ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ጊዜ፡ ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ከ08/11/2018 ዓ.ም እስከ 28/11/2018 ዓም ይሆናል።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት፡ በ29/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሜዴክስ ዲያግኖስቲክስ ቢሮ (ሬስ ኢንጅነሪግ ህንፃ 4ኛ ፎቅ) ነው።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ባህርዳር ሬስ ኢንጅነሪግ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 6668 / 0947 050 435 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ድርጅቱ
Tender details
- Deadline: 2026-08-04
- Publishing entity: Medex Diagnostics PLC
- Bid document price: 2,000.00 ብር
- Published: Jul 15, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.