Legal, procurement and compliance advisory

አራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተገቢውን ምዝገባ ማድረግ (Undertaking Registration) እና የአክሲዮን ካፒታሉን ማሳደግ (Intending to raise capital) ማስደረግ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን አራዳ አትክልት ተራ የገበያ ማዕከል አ.ማ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባስቀመጠላቸው መስፈርት መሠረት አክሲዮን ማህበራት ድርጅታቸውን እንዲያስመዘግቡ ይደነግጋል። በመሆኑም አክሲዮን ማህበራችን በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተገቢውን ምዝገባ ማድረግ (Undertaking Registration) እና የአክሲዮን ካፒታሉን ማሳደግ (Intending to raise capital) ማስደረግ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተፈቀዳላቸው የካፒታል ገበያ አማካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ እንዲሳተፉ ይጠይቃል።

ተጫራቾች የሚከተሉት መስፈርት አቅርበው መወዳደር ይችላሉ፣

1. ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ተገቢውን የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤

2. ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤

3. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ፤

ተጫራቾች ድርጅታችሁን ማንነት የሚገልፅ (Company Profile) ጋር የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ፕሮፓዛላቸውን አያይዘው በሰም በታሸገ ኤንቭሎፕ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ጨረታው ነሐሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 8፡00 ሰዓት በአ.ማ ቢሮ ይወጣል።

አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ ህጋዊ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊስም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 35 40 15 95/96 ማግኘት ይቻላል

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ክ/ከተማ አራዳ ወረዳ 1 የቤ.ቁ አዲስ ፒያሳ አትክልት ተራ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ጂ4-024


Tender details

  • Deadline: 2026-08-17
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-08-17 14:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Arada Atkilt Tera Market Center S.C.
  • Published on: Reporter (Aug 02, 2026)
  • Posted at: 2026-08-03T12:15:08.000Z
← Back to all tenders