በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ባለ5000 ሊትር የውሃ ታንከር፣ የውሃ ታንከር መስቀያ ብረት፣ የድራፍት ማሽን፣ ከዕንጨት የተሰራ የመጠጥ መደርደሪያ፣ ከዕንጨት የተሰራ ባንኮኒ፣ የስጋ መስቀያ ሜንጦ እና 1*2 አልጋ አንድ ተደራቢ ያለው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ በለሚ ኩ/ክ/ከ/ወረዳ 14 ፋይናንስ ፅ/ቤት ከአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለሚ ኩራ ምድብ ችሎት በበ/ቁ 51440 በቀን 07/11/2018 ዓ.ም በተፃፈ ትዕዛዝ መሰረት በፍ/ባለዕዳ ስም ተመዝግበው የሚገኙ ንብረቶችን ማለትም፣

  1. ባለ5000 ሊትር የውሃ ታንከር፣
  2. የውሃ ታንከር መስቀያ ብረት፣
  3. የድራፍት ማሽን
  4. ከዕንጨት የተሰራ የመጠጥ መደርደሪያ ፣
  5. ከዕንጨት የተሰራ ባንኮኒ፣ 
  6. የስጋ መስቀያ ሜንጦ
  7. 1*2 አልጋ አንድ ተደራቢ ያለው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲሳተፉ ይጋብዛል። ተወዳዳሪ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያቀረቡትን ዋጋ ¼ በጥሬ ገንዘብ(ካሽ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 ብር በመከፈል የካአባዶ ገደራ ገዛህኝ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ የዋጋ ማቅረቢያ ዋናውን እና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኢንቭሎፕ በወረዳው ፋ/ፅ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች በተገኙበት በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ለይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
  5. የጨረታው አሸናፊ ተጫራች ንብረቶችን ከ 3 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከፍለው መውሰድ አለባቸው።
  6. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊውና ለተሸናፊ በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ እንገልፃለን። ተጫራቾች ንብረቶችን በወረዳ 14 አስተዳድር በተለምዶ መስቀለኛ አካባቢ ማየት ይችላሉ።
  7. ወረዳው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፤- በስቁ. 011-866 0491 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- የካ አባዶ ገደራ ገዛኸኝ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ይገኛል

በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የወረዳ 14 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-03 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lemi Kura Woreda 14 FEDB
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jul 16, 2026
  • Posted at: 2026-07-16T08:09:10.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders