ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ ዲስትሪክት የእርሻ ትራክተር ከነማረሻው መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ዱንጎ ጅሬኛ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንሲንግ አሰራር መሰረት የተከራየውን የእርሻ ትራክተር በኪራይ ውሉ መሰረት መከፈል ባለመቻሉ ምክንያት ባንኩ አንድ የእርሻ ትራክተር ከነማረሻው መልሶ የተረከበው ሲሆን ትራክተር ከነ ማረሻው ባለበት እንዲሸጥ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ውሳኔ አስተላልፏል። ስለሆነም ንብረቱን መግዛት የሚፈልግ ተጫራች ከታች በተዘረዘረው መረጃው መሰረት በጨረታው ቀን በአካል ተገኝቶ መሳተፍ ይችላል።
|
ተ.ቁ |
የተከራይ ስም |
በሐራጅ የሚሸጠው ንብረት የሚገኝበት ቦታ |
የንብረቱ ዝርዝርና አይነት |
የጨረታው መነሻ ዋጋ (ብር) |
የጨረታው ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ዱንጎ ጅሬኛ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ
|
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን፣ ወሊሶ ከተማ፤ ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወሊሶ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
-የእርሻ ትራክተር(Landini Agricultural Tractor-112hp): ብዛት 1/አንድ/ -ማረሻ(OTMA O/OD70/E4): ብዛት 1/አንድ |
2,650,000
|
2ኛ ዙር
|
ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 03:00-6:00
|
የጨረታው ማሳሰቢያዎች
- ከላይ የተመለከተውን ንብረት መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታው የመነሻ ዋጋ 1/4ኛ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ በማቅረብ በሀራጁ ላይ መሳተፍ ይችላል።
- ሐምሌ 1/2018 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተላለፈውን ትዕዛዝ መሰረት ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወሊሶ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይከናወናል።
- በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በባንኩ ተረጋግጦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
- አሸፊው ተጫራች ቀሪዉን ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል።
- በሀራጁ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል(ግለሰቦች፣ ተቋማት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ያለው ከሆነ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፤ ባይሆን ከንብረቱ የሚፈለገውን የጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ ይከፍላል።
- የሀራጁ አሸናፊ የንብረቱን የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተ.እ.ታ (VAT) ጨምሮ የመክፈል ግዴታ አለበት።
- ስለ ንብረት ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚፈልግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት በስልክ ቁጥር +251 11 558 8368 ደውሎ ማነጋገር ወይም ኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወሊሶ ቅርንጫፍ ቀርቦ ንብረቱን ማየት ይቻላል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደቡብ ምዕራብ ዲስትሪክት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-07-24
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 16, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.