ግዮን የፕላስቲክ ዉጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ ማህበር ለቢራ ካሳ፣ ወንበርና ጠረጴዛ ማምረቻ የሚሆን ጥሬ እቃ /HDPE PPcopolymer, Different color master batch/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/ግ/2018
ግዮን የፕላስቲክ ዉጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ ማህበር ለቢራ ካሳ፣ ወንበርና ጠረጴዛ ማምረቻ የሚሆን ጥሬ እቃ /HDPE PPcopolymer, Different color master batch/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ክፈያ መለያ ቁጥር /ቲን/ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸዉን የሚያሳይ ማስረጃ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
2. ተዋዳዳሪዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋጋጥ ከዋናው ጋር የተገናዘበ የምስክር ወረቀት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ በሲፒኦ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ።
4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወይም በባህርዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚገኘዉ ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ወይም በ DHL በድርጅቱ አድራሻ መላክ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ክፍት ሆኖ በቀጣዩ ቀን 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በባህር ዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በሚገኘዉ ግዮን የፕላስቲክ ዉጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/ የግ ማህበር ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት ቀን ክብረ በዓል ከሆነ ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
6. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዮን የፕላስቲክ ዉጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባህር ዳር ከተማ አጼ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583210046 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. የመጫረቻ ሰነዱን ባህር ዳር ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቢሮ ቁጥር 5 በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት ማግኘት ይችላሉ፡፡
ግዮን የፕላስቲክ ውጤቶች ማምረቻ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ክፍት ሆኖ በቀጣዩ ቀን 3፡30
- Bid opening: 2026-08-17 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ክፍት ሆኖ በቀጣዩ ቀን 4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ghion Plastic Products Manufacturing P.L.C.
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 17, 2026
- Posted at: 2026-07-17T08:19:49.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.