የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ጽ/ቤት በአምዋጭ ስደተኛ ሳይት ዳባት ከተማ እና በአፍጥጥ ስደተኛ ሳይት ገዳውሃ ከተማ በሚገኘው በስደተኛ ሳይቱ መጋዘን የሚገኘውን ሲሚንቶ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የወጣ የስሚንቶ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ ለተአ/ዳባት/002/2018

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ጎንደር ቅ/ጽ/ቤት በአምዋጭ ስደተኛ ሳይት ዳባት ከተማ እና በአፍጥጥ ስደተኛ ሳይት ገዳውሃ ከተማ በሚገኘው በስደተኛ ሳይቱ መጋዘን የሚገኘውን ሲሚንቶ ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ባወጣው የዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-

1) ተጫራቾች የተዘጋጀውን የሽያጭ ጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በጎንደር ቅ/ጽ/ቤት እና በአፍጥጥ ስደተኛ ሳይት በሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት መ/ቤት ቅጥር ግቢ አስተዳደርና ፋይናንስ ቢሮ በመገኘት እና ክፍያ በመፈጸም ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ከሐምሌ 10 እስከ 24/2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።

2) በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት/Refugees and Returnees Service /በሚል የተዘጋጀ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ የባንክ ዋስትና /Bank Guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3) ማንኛውም ተጫራች ከሐምሌ 10 እስከ 24/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጎንደር ቅ/ጽ/ቤት እና ገንዳውሃ በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ በመገኘት ዕቃዎቹን መመልከት ይችላል። ቅዳሜና እሁድ የስራ ቀናት አይደሉም።

4) ጨረታው ጎንደር ከተማ አምባራንስ ሆቴል በሚገኘው የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ የሚካሄድ ሲሆን የጨረታው ሳጥን ሐምሌ 24 ከቀኑ 7፡30 ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።

5) የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያሰያዙት ሲፒኦ ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ያሰያዙት የጨረታ ዋሰትና በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

6) ተጨራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን መረከብ አለባቸው።

7) በተራ ቁጥር 6 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጨራች ለጨረታው ማስከበርያ ያስያዘው ሲፒኦ ለአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ገቢ በማድረግ የተሻለውን አማራጭ የመውሰድ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8) አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9) ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251913871445 ወይም 251910048505 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-31
  • Bid closing time: 13:30
  • Bid opening: 2026-07-31 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Refugee and Returnee Service
  • Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jul 17, 2026
  • Posted at: 2026-07-17T08:30:24.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders