የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ እቃዎች በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በ ቀን 15/11/2018 ዓ/ም እና 18/11/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ፡ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት፡ እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልግ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት፣በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15/11/2018 ዓ/ም እና 18/11/2018 ባሉት ቀናት ለግልፅ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ ።

3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100.000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

.ቁ

የጨረታ ቦታ

የጨረታ አይነት

ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች

 

ዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

ቃሊቲ ጉምሩክ

ግልጽ እና ሃራጅ

ጫማዎች፣ አልባሳት፡ ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋወጫ ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ተሸከርከሪ መኪናዎች፣ የሞባይል ቀፎ እና አክሰሰሪ ምግብ ነክ፣ጥቅል ብረት፣ቆርቆሮ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልጽ ጨረታ እስከ15/11/18 ዕረብ እና 18/11/2018 ቅዳሜ ጠዋቱ 3፡45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 4፡45

ለግልጽ ጨረታ እስከ 15/11/18 ዕረብ እና 18/11/ 2018 ቅዳሜ ጠዋቱ 3፡45 እና ሃራጅ ጨረታ እስከ 5፡00

5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን  ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።

8. ከላይ በተ.ቁ7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-224-14 02 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-25
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-07-25 11:00
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Awash Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jul 17, 2026
  • Posted at: 2026-07-17T09:04:18.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders