የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በነቀምት ከተማ በድርጅቱ መጋዘኖች ተከማችቶ የሚገኝ በአሶሳ አካባቢ የተመረተ ከዘርነት የተረፈ ለምግብነት የሚውል ንፁህ የቦቆሎ እህል ለሁለተኛ ጊዜ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 010/ሽያጭ/18 ዓ.ም
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በነቀምት ከተማ በድርጅቱ መጋዘኖች ተከማችቶ የሚገኝ በአሶሳ አካባቢ የተመረተ ከዘርነት የተረፈ ለምግብነት የሚውል ንፁህ የቦቆሎ እህል ለሁለተኛ ጊዜ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፉና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታው ውድድር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 600,000 /ስድስት መቶ ሺህ የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው ሰነድ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 400 በመክፈል በሀዋሳ ከተማ በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ ኤንቨሎፕ/ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ን/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።
PARC - የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጐ በእለቱ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ ስብሰባ አደራሽ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል።
- ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በስልክ ቁጥር 046 220 1752/2285/2117
ሀዋሳ
የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-07-27
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-27 14:30
- Bid opening (note): የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Southern Seeds Enterprise
- Bid bond: 600,000 (ስድስት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published: Jul 18, 2026
- Posted at: 2026-07-18T07:21:30.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.