የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የ2019 በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አ/ቃ/ፐ/001/2019

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የ2019 በጀት አመት አንደኛ ዙር ጥቅል ግዥ 

የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሠ/ሀ/ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን በስሩ ለሚገኙ ሴክተር ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት የሚያስፈልጉ የተለያዩ የአገልግሎት እና የእቃ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1. ከ40_60 የመያዝ አቅም ያለው የህዝብ አገልግሎት የሚሰጥ የተሸከርካሪ ኪራይ
  • ሎት 2. 50 ኩንታል የመያዝ አቅም ያለው የጭነት የተሽከርካሪ ኪራይ
  • ሎት 3. 12 ሰው የመያዝ አቅም ያለው ሚኒባስ የተሸከርካሪ ኪራይ
  • ሎት 4. የተለያዩ የህትመት ስራዎች
  • ሎት 5. የተለያዩ ዲኮሮች፤ የተለያየ መጠን ያላቸው ድንኳኖች እና የመድረክ ከፍተኛ፣ እና አነስተኛ እስቴጆች ከነምንጣፋቸው እንዲሁም የመድረከ ስከሪን ግራና ቀኝ የሚገጠም፡
  • ሎት 6. 1ኛ ደረጃ ፣2ኛ ደረጃ ፣ 3ኛ ደረጃ ክሪስታል ዋንጫዎች እና ወርቃማ ዋንጫዎች
  • ሎት 7. የከባድ መኪና (ተሽከርካሪ) ጥገና
  • ሎት 8.የፎቶ ፍሬም
  • ሎት 9. የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች
  • ሎት 10. የተለያዩ የተሽከርካሪ የመካከለኛ እና ከባድ ተሸከርካሪዎች ጎማ
  • ሎት 11. የተለያዩ የተሽከርካሪዎች ባትሪ
  • ሎት 12. የተሽከርካሪ አልባሳትና ጌጣ ጌጥ
  • ሎት 13. የኤሌክትሪክ እቃዎች
  • ሎት 14. ለጄኔሬተር ጥገና የሚያስፈልጉ የመለዋወጫ እቃዎች
  • ሎት 15. ለጄኔሬተር ጥገናና ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ
  • ሎት 16. ለህንጻ እና ለጊቢ ማስዋብ አገልግሎት የሚያስገልጉ የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 17. የቀላል መኪና (ተሽከርካሪ) ጥገና

የሲፒኦ መጠን

  • ሎት 1. 20,000 (ሃያ ሺህ)
  • ሎት 2. 20,000 (ሃያ ሺህ
  • ሎት 3. 20,000 (ሃያ ሺህ
  • ሎት 4. 20,000 (ሃያ ሺህ)
  • ሎት 5. 20,000 (ሃያ ሺህ)
  • ሎት 6. 20,000 (ሃያ ሺህ)
  • ሎት 7. 70,000 (ሰባ ሺህ)
  • ሎት 8. 15,000(አስራ አምስት ሺህ)
  • ሎት 9. 20,000 (ሃያ ሺህ)
  • ሎት 10. 30,000 (ሰላሳ ሺህ)
  • ሎት 11. 20,000 (ሃያ ሺህ)
  • ሎት 12. 20,000 (ሃያ ሺህ)
  • ሎት 13. 40,000 (አርባ ሺህ)
  • ሎት 14. 60,000 ስልሳ ሺህ)
  • ሎት 15. 60,000 (ስልሳ ሺህ)
  • ሎት 16. 30,000 (ሰላሳ ሺህ)
  • ሎት 17. 50,000 (ሃምሳ ሺህ)

CPO ሲያስሩ ለኢቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ብለው ያሰሩ

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

1.ለስራዉ ህጋዊ የታደሠ ንግድ ፈቃድ ኖሮአቸዉ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣የአቅራቢነት ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይ መሊያ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክርት ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ጽ/ቤቱ ስርዝ ድልዝ ሰነድ የማይቀበልና ከዉድድር ዉጪ የሚያደርግ መሆኑን እናሳውቃለን።

3. ተጫራቾች የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ካደራጃቸው አካል 6 ወር ያላለፈው የድጋፍ ደብዳቤ በማቅረብ በነፃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በፐ/ሰ/የሰ/ሀል ፅ/ቤት የግዥ አስተዳደር ቡድን 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መሙላት ያለባቸው ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናል ላይ ኦርጅናል ኮፒ ላይ ኮፒ በማለት እያንዳንዱን ሎት ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ አየር ላይ በማዋል በአስራ አንደኛው የስራ ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ተጫራቾች ሰነድ በማስገባት 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 508 ጨረታው ይከፈታል።

5. ተጫራቾች ሰነድ ሲመልሱ ናሙና (ሳምፕል) እንዲያቀርቡ በተጠየቁባቸው የአገልግሎት ወይም የእቃ ግዥ ላይ ናሙና የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን የሚቀርበው ናሙና ምንም አይነት ማንነታችሁን የሚገልፅ መረጃ እንዲኖርበት አይፈቀድም።

6.ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ግዥ ፈጻሚው አካል ባዘጋጀው ስነድ ላይ ብቻ መሙላትና በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የድርጅታቸውን አድራሻስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በመመሪያውና በጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረቡት የመወዳደሪያ መስፈርቶች ብቻ ይሆናል።

8. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  • ለተጨማሪ መረጃ፡- አድራሻ፡- ከቃሊቲ መናኽሪያ ፊት ለፊት ባለው የአስተዳደሩ ህንፃ ላይ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 508 መጠየቅ ይቻላል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የግዥ አስተዳደር ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-07-30
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-30 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Akaki Kality k/ketema public human resource office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jul 18, 2026
  • Posted at: 2026-07-18T07:57:59.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders