በአብክመ የኦሮ/አስ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል 5/ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ለአንድ ዓመት የሚቆይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በአብክመ የኦሮ/አስ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል 5/ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ለአንድ ዓመት የሚቆይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፦
የእቃዎች ዝርዝር በየሎቱ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡-
- ሎት 1 የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባቶች
- ሎት 2 የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች
- ሎት 3 የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች
- ሎት 4 በኪሎ ሜትር የሚቀየሩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ሲሆኑ
መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ስንገልጽ -
1/ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
2/ ተጫራቾች የምዝገባ የምስክር ወረቀት /Tin No/ ማቅረብ የሚችል
3/ ግዥው ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
4/ ተጫራቾች ለሚያቀርቡት/ለሞሉት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ማለትም በሎት 1 ለተጠቀሰው እቃዎች 30,000 ብር በሎት 2 ለተጠቀሰው እቃዎች 50,000 ብር በሎት 3 ለተጠቀሰው እቃዎች 100,000 ብር በሎት 4 ለተጠቀሰው እቃዎች 30,000 ብር በባንክበተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ወይም በገቢ ደረሰኝ ወይም በመ/ቤታች የመደበኛ በጀት ማስፈፀሚያ ኢት.ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000160693766 በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋናው ኦርጅናል የመወዳደሪያ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5/ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ የያዘ ከአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 /አስራ አምስት ቀናት ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
6/ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት እለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀነ- 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4:30 ሰዓት የሚከፈት መሆነን ስንገልጽ ነገር ግን የመክፈቻው ቀን በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
7/ መ/ቤቱ የተሻለ ነገር ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8/ የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉትን እቃዎች በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግቢ ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
9/ ለበለጠ መረጃ ከተጫራቾች መመሪያ ላይ መረዳት ይቻላል ወይም በስልክ ቁጥር 09 10 37 87 37 እና 09 12 03 93 15 በመደወል መጠየቅና መረዳት ይቻላል።
10/ መ/ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በጥቅል ወይም በሎት የምናወዳድር መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሻችን ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መንገድ 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛ።
አብክመ በኦሮሞ አስ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት እለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-03 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት እለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Aretuma Faresi Woreda FEDB Office
- Buyer address: ጨፋ-ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 300 ኪ/ሜ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Jul 18, 2026
- Posted at: 2026-07-18T08:05:03.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.