የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት እ.ኤ.አ በ2026 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውል የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች (ፎቶ ኮፒ ማሽን እና ፕሪንተር፣ ዓርማ የሚታተምባቸው ቲሸርቶች፣ እስከሪብቶ፣ አጀንዳ እና ሌሎችም) ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ስተአ/005/2026
የአገልግሎት መ/ቤታችን እ.ኤ.አ በ2026 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውል የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች (ፎቶ ኮፒ ማሽን እና ፕሪንተር፣ ዓርማ የሚታተምባቸው ቲሸርቶች፣ እስከሪብቶ፣ አጀንዳ እና ሌሎችም) ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
|
ተቁ |
የሎት(lot) ቁጥር |
የዕቃዎቹ ዓይነት |
የጨረታ መለያ ቁጥር |
|
1 |
ሎት አንድ |
Heavy Cotton T-Shirt, Branded Pen, Document folder (PP)Executive Notebook (Journal) and offshell Jacket (Vest/Jacket Combo) |
ስተአ/005/1/18 |
|
2 |
ሎት ሁለት |
Print Copy, scan, Fax, color Print All-in- One Machine with original Cartridge/Toner and Heavy Duty -print, copy, scan Stapling File with document feeder All in-one-Office Machine |
ስተአ/005/2/18 |
በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም የመንግሥት ግብር አጠናቅቀው ለመከፈላቸው ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ፣የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ በጨረታ ለመሳተፍ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን በአቅራቢነት የተመዘገቡ እንዲሁም የተ.እ.ታ. ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን፣ በብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ውል በመግባት የሚፈፀም ይሆናል።
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
1) የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ አራዳ ክፍለከተማ ወረዳ 4 እንቁላል ፋብሪካ ወይም የፌዴራል ፖሊስ ክብብ ፊት ለፊት ከሚገኘው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና መ/ቤት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመምጣትና የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ለ10 ተከታታይ ስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት፣ ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ባለው ጊዜ ውስጥ መግዛት ይቻላሉ። ቅዳሜና እሁድ የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ስራ ቀናት አይደሉም።
2) ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጥቅል ዋጋ 2/ሁለት/ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በF.D.R.E Refugees and Returnees Service ስም በተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በቅድመ-ሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ዋስትና ደብዳቤ፣ የአገልግሎቱን ዋጋ፣ በቀረበው ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ መሰረት የቴክኒክ ሰነድ እና እንዲሁም በጨረታ ሠነዱ የተዘረዘሩትን የብቃትና የልምድ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚያያዙ ማስረጃዎች በሙሉ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላበቃላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
3) የመጫረቻ ሠነዳቸውን ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 10ኛው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ከታች በተመለከተው አድራሻ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን፤ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የሰራተኞች ክበብ ምድር ቤት ይከፈታል። ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ፣ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
4) መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ
ከፌዴራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 09-97-23-66-31
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-07-29
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 10ኛው የስራ ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-29 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 10ኛው የስራ ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Refugee and Returnee Service
- Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 18, 2026
- Posted at: 2026-07-18T08:23:24.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.