Amharic

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የሚገኝ በሴቶች ፎረም የሚተዳደረውን ካፍቴሪያ በግልጽ ጨረታ በማውጣት ማከራየት ይፈልጋል

Description

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ የሚገኝ በሴቶች ፎረም የሚተዳደረውን ካፍቴሪያ በግልጽ ጨረታ በማውጣት ማከራየት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የመወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጂቶችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

1. የጨረታ ሰነዱ ዓላማ ብቁ እና ህጋዊ የሆኑ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና በዘርፉ በቂ ልምድና ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎችን በጨረታው እንዲሳተፉ መጋበዝ ነው።

2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከሆስፒታሉ ግዥ ክፍል በመግዛት መሳተፍ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የመጫረቻ ዋስትና በሆሰፒታሉ ስም ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሰፒኦ ብቻ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

4. ጨረታው የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዥ ክፍል ውስጥ አየር ላይ ከዋለበት ተከታታይ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 በይፋ ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

5. መስሪያ ቤቱ የውሃ እና የመብራት ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል።

6. ተጫራቹ ድርጅት የጨረታው መዝጊያ ከመድረሱ 2 ቀናት በፊት በማንኛውም የስራ ሰዓት የካፍቴሪያ ቦታውን መጎብኘት እና ግልጽ ያልሆኑ ነገሮችን በአካልም ሆነ በጽሁፍ ግልጽ እንዲሆንለት መጠየቅ ይችላል።

7. አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት አዋርድ ከተሰጠበት ቀን ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ አገልግሎቱን መስጠት መጀመር ይኖርበታል።

8. ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ፋይናንሺያል ኦርጂናል እና ኮፒ ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ፖስታ ግልጽ ሆኖ በሚታይ መልኩ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

9. ሆስፒታሉ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-28 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: St. Peter Specialized Hospital
  • Buyer address: ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሽሮ ሜዳ ከፍ ብሎ ቁስቋም ቤተክርስቲያን ሳይደርስ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jul 19, 2026)
  • Posted at: 2026-07-20T08:07:32.000Z
← Back to all tenders