የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለዩኒት ፕሮዳክሽን የምርት አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለዩኒት ፕሮዳክሽን የምርት አገልግሎት ከተለያዩ ድርጅቶች ግለሰቦች ጋር ውል በመግባት የተለያዩ መገልገያ ማቴሪያሎችን/ ቁሳቁሶችን እያመረተ እና ለተጠቃሚ/ ለገበያ እያቀረበ መሆኑ ይታወቃል።
ስለሆነም ለዚሁ ስራ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
1ኛ. በዘርፉ የተሰጠ እና ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ።
2ኛ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው እና ማቅርብ የሚችሉ።
3ኛ. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያለው እና ማቅርብ የሚችሉ።
4ኛ. የተጨማሪ እሴት ታክስ/ት ተመዝጋቢ የሆነ እና ማቅርብ የሚችሉ።
5ኛ. የአንዱን ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር እና ትራንስፖርቱን ጨምርው በመሙላት ወደ አሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማቅርብ የሚችል።
6ኛ. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት እለት/ቀን/ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ብቻ በቤ/ጉ/ክ/መ/ አሶላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 2 በመደበኛ የመንግስት የስራ ስዓት በአካል በመቅርብ የእቃውን ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ በ 300 ብር በመግዛት መወዳደር ይቻላል።
7ኛ. ተጫራቾች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያቸው ላይ የድርጅታቸውን ስም ሙሉ አድራሻቸውን ስልጣን በተሰጠው የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማቸውንና ህጋዊ ክብ ማህተማቸውን በመምታት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ድረስ ብቻ ዋጋውን ሞልተው ማቅርብ የሚኖርባቸው ሲሆን ኮሌጅ ካቀረበው የዋ ጋ መሞያ ሰንጠረዥ ውጭ ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ተቀባይነት አይኖረውም። በ11ኛው ቀን የሚከፈት ሁኖ ቀኑ በዓል ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ጨረታው ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨርታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
7ኛ. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 057-775-1720/299
/+251917458131/+251910412334 ደደውሉ።
የአሶሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-07-31
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00
- Bid opening: 2026-07-31 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30
- Region: Beneshangul Gumuz
- Publishing entity: Assosa Poly Technique College
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jul 21, 2026
- Posted at: 2026-07-21T08:10:37.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.