ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ. የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጎማዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር Gada/NCB/01/2018

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ኢማ የተለያዩ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ጎማዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በሟሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ እንዲሁም ንግድ ምዝገባ ምስክር እና ሌሎች አሰፈላጊውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሲሆን ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 2፡30 እሰከ 11፡00 በመምጣት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር  በመክፍል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና በመፈርም በሰም በታሸገ ፓስታ ማቅረብ ይኖርበታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የሞሉትን ጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው
  5. የጨረታ አሸናፊነቱ ከተረጋገጠ ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት የዋጋውን ውል ማስከበሪያ 10 % በማስያዝ ውል መፈረም ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራች በሚያቀርቡት ዋጋ የጨረታ መግቢያ ሰዓት ከተጠናቀቀ በኋላ ማሻሸያ ማድረግ እና እራሳቸውን ከጨረታ ማግለል አይቻልም
  7. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተረሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም
  8. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰረዘ እና የተደለዘ ሆኖ ለመለየት የሚያስቸግር ዋጋ ተቀባይነት የለውም
  9. ለተሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ ከአሸናፊ ተጫራቾች ጋር ውል እንደተፈጸመ ተመላሽ ይሆናል።
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታ ማስታወቅያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን አየር ላይ የሚውል ሆኖ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  11. የጨረታ መክፈቻ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  12. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ - ሰንጋ ተራ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፌት ቢፍቱ አዱኛ ህንጻ 12ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011-558-25-19

ገዳ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-05
  • Publishing entity: Geda Transportation P.L.C.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jul 21, 2026
  • Posted at: 2026-07-21T08:32:59+00:00

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders