Disposal, scrap and surplus sales
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ ዕቃዎች በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር -02/2019 ዓ.ም.
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ቶንዶስ፣
- አልባሳት፣
- ተሽከርካሪ፣ ጫማ እና
- ወንበር /office chair/ በግልፅ እንዲሁም
- ጫማ፣
- የምግብ ጨው እና
- dorco/ምላጭ/ በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል።
- የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊዮን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርትፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም።
- በጨረታ የሚሸጠው ዕቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኢንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሐራጅ ጨረታው 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል።
- ተጫራቾች ለዕቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል።
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ ዕቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ ዕቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሐራጅ ጨረታ የዕቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እንዲሁም የዕቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን ብር በታች ለሆነ ዕቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000 (መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 033 551 0693 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-27
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-27 10:30
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: Revenue and Custom Commission Kombolcha Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 21, 2026)
- Posted at: 2026-07-21T09:31:07.000Z