የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ አስ/ር ቢሮ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ መሳሪያዎች አወዳድሮ በሎት በጥቅል መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ አስ/ር ቢሮ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ 

  • ሎት 1. የታቡራታ በር እና
  • ሎት 2. የህንፃ መሳሪያ አወዳድሮ በሎት በጥቅል መግዛት ይፈልጋል፡፡

 በዚህም መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር  ይችላሉ፡፡

  1.  ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ፈቃድና የቲን ተመዝጋቢ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ስለ እቃው የተዘጋጀውን (ስፔስፊኬሽን) በትክክል በማጥናት በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ የአንዱንና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል መሙላት አለባቸው ሥርዝ ድልዝ ያለበት ዋጋ ማቅረቢያ በተወዳዳሪው ልዩ ፊርማ መረጋገጥ አለበት፡፡
  3.  በዋጋው ማቅረቢያ ላይ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ስም፣ ፊርማና የድርጅቱ አርማ ያለው ማህተም መኖር አለበት፡፡ በተጨማሪ በፖስታው ላይ ያጫራቹን መ/ቤት ስምና የራሳቸው አድራሻ በትክክል ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  4.  በሌላው ዋጋ ተንተርሶ መወዳደር አይፈቀድም፡፡
  5. የሞሉት ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ፖስታ ላይ የንግድ አድራሻውንና ስሙን በመግለጽ በደንብ በታሸገ ፖስታ በማሸግ የሞላዉን ዋጋ ኦርጅናል ፖስታ የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥ ን/አስ/ቡድን ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ከቀረበዉ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ በመሂ 1 ወይም ቢድ ቦንድ በማስያዝ በፖስታዉ ዉስጥ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ከጨረታዉ ይሰረዛሉ፡፡
  8. በጨረታው ለተሸነፋ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ገንዘብ የጨረታው አሸናፊ ተለይቶ ውል ከወሰደ በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
  9. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉ 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የዉል ማስከበሪያ ካሸነፈዉ ከጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በመሂ 1 በማስያዝ ዉል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10.  በጨረታው ውድድር ወቅት ቅር የተሰኙ ተጫራቾች አሸናፊው በተገለጸ እለት 5 የሥራ ቀናት ቅሬታውን ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች ያለ በቂ ምክንያት ውሉን ካፈረሰ ያስያዘውን ገንዘብ በመቀጫ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ በህግም እንዲጠየቅ ይደረጋል፡፡
  12.  የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ውድድር ጥያቄ ወይም ማስተካከያ ተቀባይነት የለውም ማስተካከል የሚቻለው ጨረታው ከመከፈቱ ከ2 ቀን አስቀድሞ ማስተካከል ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ አስቀድሞ ከጨረታው መውጣት የሚችሉ ቢሆኑም ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም፡፡
  14.  በጨረታ ሰነዱ የተካተቱ ማንኛውም ሰነዶች ገንጥሎ ማስቀረት አይፈቀድም፡፡ ይህንኑ ችላ በማለት ተገንጥሎ የቀረበ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፣ ለጨረታው መጓተት በር የሚከፍት በመሆኑ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስም፡፡
  15.  የጨረታ ሰነዱ ሙሉ ገጽ መሆኑን ማረጋገጥ ከገዥ ይጠበቃል፡፡
  16. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳችውን ማግለል አይችሉም፡፡
  17.  ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑ ለወደፊቱ በመንግስት ግዥ በጨረታ እንዳይሳተፍ እንደሚያደርግና ያስያዙት ገንዘብ እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  18. ማንኛውም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ላይ ይቆያል፡፡
  19.  ጨረታው በ16 ተኛው ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  20. መ/ቤቱ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. የጨረታ ሠነዱን ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  22. የማስረከቢያ ቦታ ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ንብረት ክፍል ማስረከብ የሚችሉ፡፡
  23. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  24. ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልገዎ በስልክ ቁጥር 058 229 00 50 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-04 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ተኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Guagusa Shekudad Woreda FEDB
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published: Jul 20, 2026
  • Posted at: 2026-07-21T10:46:35.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders