በጥቅል 50/ሀምሳ/ በግምት ሃያ አምስት ቶን የሚሆን 3 ሚሊ ሜትር ዲያ ሜትር ያለው ሽቦ ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
- አፈ/ከሳሽ………………አማራ ህንፃ ስራዎች ኮንስትራክሽን
- አፈፃፀም ተከሳሽ…….ይፋት ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
መካከል ባለዉ የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ፤ በባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አዲስ አለም ቀበሌ ሸኔል ሆም የተገጣጣሚ ህንፃ ማምረቻ ፋብሪካ ከሚገኘው መጋዘን ውስጥ የሚገኝ የአፈፃፀም ተከሳሽ ንብረት የሆነ በጥቅል 50/ ሀምሳ/ በግምት ሃያ አምስት ቶን የሚሆን 3 ሚሊ ሜትር ዲያ ሜትር ያለው ሽቦ የመነሻ ዋጋውን ሳይጠብቅ በአፈ/ተከሳሽ ስም የተመዘገበዉን ሽቦው በሚገኝበት አድራሻ በባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አዲስ አለም ቀበሌ ሸኔል ሆም የተገጣጣሚ ህንጻ ማምረቻ ፋብሪካ መጋዘን ውስጥ በግልጽ ጨረታ የመነሻ ዋጋውን ሳይጠብቅ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ በጨረታ እንዲሸጥ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ትዕዛዝ በሰጠው መሰረት የባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት አንድ ሰው ታዛቢ በመመደብ የባህርዳር ከተማ 5ኛ ፖሊስ ጽ/ቤትም ፀጥታውን የሚያስከብር አንድ ሰው በመመደብ የጨረታው ስነ-ስርዓት በአግባቡ እንዲከናወን እንዲደረግ ሆኖ የአብከመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሐራጅ ባይም ጨራታውን በበላይነት በመምራት ጨራታው ይካሄዳል።
ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ማንኛውም ሰው ከቦታው በመገኘት ምልከታ አድርጐ ቀርቦ ህጋዊ መታወቂያ በመያዝ መጫረት መሳተፍ የሚቻል ሲሆን ከተጫራቾች በኩል ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ አሸናፊ ሲሆን እና አሸናፊው እንደታወቀ ያሸነፈበትን ገንዘብ ከተቻለ ሙሉውን ገንዘብ የሚያስይዝ ካልተቻለም አንድ አራተኛውን ወዲያውኑ ማስያዝ የሚችል መሆኑን እንዲያውቁት የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት አዟል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-05
- Publishing entity: ANRS Supreme Court
- Published: Jul 22, 2026
- Posted at: 2026-07-22T08:10:42.000Z
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.