አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ተለያዩ ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር:- አ/ድ/ማ/ፋ/ብ/ግ/ - 01/2019
አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ተለያዩ ዓይነት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
- (ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ዮፒኤስ፣ ኤሌክትሪክ ዲቫይዳር እና ሌሎች) እና
- የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን (የተለያየ አግዳሚ ወንበር፣ ፋይል ካብኔት፣ ማናጀራል ጠረጴዛ፣ የሙያተኛ ጠረጴዛ እና ሌሎች)
በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተእታ ተመዝገቢነት የምስክር ወረቀት እና መለያ ቲን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡበት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ ቅደም ተከተል መሰረት ቫትን ጨምሮ ነው።
- ተጫራቾች ለየሎቱ የሚጫረቱበትን አጠቃላይ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) የጨረታማስከበሪያ በድርጅታችን በአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ በሚል ባንክ ጋራንቲ ቦንድ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
- አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ በፍፁም የተከለከለ ነው።
- ተጫራቾች ለሎት-1 የሚጫረቱበትን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለያይተው ማቅረብ አለባቸው። ቴክኒካል ሰነዳቸው ውስጥ በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው መሰረት ሲሆን ይሄ ካልሆነ ያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
- ተጫራቾች ለሎት2 የሚጫረቱበትን ሰነዳቸውን በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው መሰረት ማቅረብ አለባቸው ይሄ ካልሆነ ያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ብቁ የሚሆነው በዝርዝር የተቀመጠውን የጨረታመመሪያ ሲያሟሉና በጨረታ መመሪያ መሰረት ሲያቀርብ ነው። የጨረታ መመሪያ ያላሟላ ተጫራች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታ ውድድር ውጪ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉበትን እቃዎች ከእስቶራቸው ወዲያውን ማቅረብ እንደሚችሉ በመወዳደሪያ ሰነዳቸው ላይ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ለማግኘት 1,000.00 (አንድ ሺ ብር) ብቻ በአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በሚል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000735396912 በማስገባት ኦሪጂናል ደረሰኝ ብቻ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ከጦር ኃይሎች አደባባይ በስተቀኝ በኩል OLA ማደያ አጠገብ ገባ ብሎ የሚገኝ የመከላከያ ህንፃ ውስጥ ምድር ላይ ይገኛል።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ውሎ በ10ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ታሽጎ በ5፡00 ሰዓት ይከፈታል። ለጨረታዎቹ ዕለቱ ሰንበት ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
- አድራሻ ቦታ ከጦር ኃይሎች አደባባይ በስተቀኝ በኩል OLA ማደያ አጠገብ ገባ ብሎ የሚገኝ የመከላከያ ህንፃ ውስጥ ምድር ስልክ ቁጥር፡- 011-385-1613/ 09 11 80 53 16።
- አክሲዮን ማህበሩ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ.
Tender details
- Deadline: 2026-07-31
- Publishing entity: Adwa Dil Microfinance Institution S.C.
- Bid bond: 2% ለየሎቱ
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published: Jul 22, 2026
- Posted at: 2026-07-22T08:55:37.000Z
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.