Disposal, scrap and surplus sales

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዞው እና ተወርሰው የሚገኙ ዕቃዎች መኪናን ጨምሮ በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 43/2018

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዞው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከሪካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት ዕቃዎች፤ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች፤ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፤ ነዳጅ፤ ምግብ ነክ ዕቃዎች፣ የጥራጥሬ እህሎች እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች መኪናን ጨምሮ በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፊቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

2. ተጫራቾች የግልጽ እና ሃራጅ ጨረታ ሰነድ በተሌግራም አካውንት የሚላክላችሁ ሲሆን ተጫራቹ ለመግዛት የሚፈልገውን የዕቃ ዝርዝር ያለበት ገጽ እና የጽ/ቤቱ ማህተም ሳይቆረጥ ፕሪንት በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00- 12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ግልጽ እና ሀራጅ ሰነድ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁጥር 16 ሰነድ የገዛበትን ደረሰኝ (RV) በመቀበል ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ሌሎች ከላይ የተገለጹ አስፈላጊ ሰነዶች እንዲሁም RV (ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ) ጭምር በማያያዝ ወደ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡

3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩከ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ጨረታው የሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እስከ 7ኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መ/ጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው፡፡

6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዘግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡

7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀሚሮ የሚቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ሲቀር ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡

8. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 444 1415 / 046 444 1564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ)
  • Bid opening: 2026-08-03 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት)
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Moyale Customs Branch Office
  • Bid bond: በግልፅ ጨረታው 5% እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T07:48:53.000Z
← Back to all tenders