Computers, laptops and workstations

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር የተለያዩ የIT እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የተለያዩ IT እቃዎች ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ HBSCITEQUIPMENT/01/0001/26

የተለያዩ የIT እቃዎች ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ሐበሻ ቢራ ፋብሪካ አክስዮን ማህበር የተለያዩ የITእቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. ሕጋዊ ምዝገባ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፣

3. በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳደሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው፤

4. ተጫራቾች ከላይ የተገለፁት መስፈርት አሟልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በአካዉንት ቁጥር 1000004335299 በመክፈል የገባበትን ስሊፕ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፤

5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ

ሀ) ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በታሸገ የጨረታ ማስከበሪያ 150,000 /አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ሌሎች ተቀባይነት ያላቸው የጨረታ ማስከበሪያዎች ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሽግ /ቴክኒካል በሚል በመለየት፤

ለ) ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በማሽግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ /ፋይናንሻል በሚል በመለየት እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤

6. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሐበሻ ቢራ አ.ማ ስም እና ከቴክኒካል ዶክመንት ኦሪጅናል አብሮ መቅረብ አለበት።

7. ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱት መስፈርቶች ሙሉ ለሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድሩ ውጭ ይሆናል

8. የጨረታው ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል

ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዳዊት ብርሃነ

የግዥ ኦፕሬሽን ክፍል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-11 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Habesha Breweries S.C.
  • Buyer address: ቦሌ ከአዲስ የልብ ህክምና ጎን/ካርጎ ፊት ለፊት
  • Bid bond: 150,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Jul 26, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T12:27:57.000Z
← Back to all tenders