Addis Ababa

ሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተየግ.ማህበር ያገለገሉ መኪኖችንና ሞተር ብስክሌቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ሜማ/15/11/18

ኩባንያችን ሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተየግ.ማህበር ያገለገሉ መኪኖችንና ሞተር ብስክሌቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላል።

1. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ሜጋ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን በአካል በመቅረብ ገርጂ ሜታ አከባቢ በሚገኘው የድርጅታችን መጋዝን በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6/12/2018 ዓ.ም ለዚህ ተብሎ በሜጋ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 217 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በስራ ስአት ማስገባት አለባቸው።

4. አንድ ተጫራች መግዛት የሚፈልገውን ከአንድ በላይ መኪና ሞተር ብስክሌት ከሆነ ለሚጫረተው ለእያንዳንዱ መኪና ሞተር ብስክሌት ዋጋ መጥቀስ አለበት።

5. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት መኪና ሞተር ብስክሌት የሚጫረቱበትን አጠቃላይ ዋጋ ሃያ አምስት በመቶ (25%) በሜጋ ማተሚያ ኃላ.የተ.የግ.ማ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዛዣ (ሲፒኦ) የጨረታ ማስከበሪያ ከጨረታው ስነድ ጋር ገቢ ማድረግ አለባቸው።

6. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ጨረታውን ላላሸነፉት ብቻ የጨረታው ውጤት እንደታወቀ ይመለስላቸዋል።

7. የጨረታው አሸናፊዎች ቀሪውን ገንዘብ በአምስት (5) የሥራ ቀናት ውስጥ አጠቃለው ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ከፍለው ንብረቱን የማያነሱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅታችን ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።

8. ጨረታው በ6/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ተዘግቶ በእለቱ 6/12/2018 ዓ.ም ልክ ከቀኑ 7፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሜጋ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል። ሆኖም የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው ከመከፈት አያግደውም።

9. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሕጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ቦሌ ፡ ሜጋ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 217
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 09 13 72 96 31
ሜጋ ማተሚያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 13:00
  • Bid opening: 2026-08-12 13:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mega Printing P.L.C.
  • Buyer TIN: 0000038949
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-27T12:41:03.000Z
← Back to all tenders