Vehicle purchase

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን የሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎት ግዥ የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መሰረት አወዳድሮ በኮንትራት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን የሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተመለከቱትን እቃዎችና አገልግሎት ግዥ የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መሰረት አወዳድሮ በኮንትራት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

  • ሎት 1፡- የተሽከርካሪ ጥገናና ሰርቪስ ፣
  • ሎት 2፡- የቀላል ተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት፣
  • ሎት 3፦ የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች
  • ሎት 4፡- ለህክምና አገልግሎት የሚውል የኦክስጅን ጋዝ አቅርቦትና
  • ሎት 5፦ የጭነት አገልግሎት 

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑንይጋብዛል።

1. ለህክምና አገልግሎት የሚውለውን የአክስጅን ጋዝ አቅርቦት በተመለከተ ተጫራቾች አምራች ካልሆኑ ምርቱን ለማከፋፈል ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸውን የውክልና ደብዳቤና ከአምራች ድርጅቱ ጋርውል የገቡበትን ሰነድ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

2. በዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣

3.ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያለው/ያላት፣

4, የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነች፣

5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

6. የሚቀርቡ አቅርቦቶች ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ዝቅተኛ ዋጋውን የሞላ ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ይሆናል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የውድድር አይነት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር /100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ /ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ 69 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ። ሰነዱን በመሙላት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን ባዘጋጀው ሳጥን በጥንቃቄ በተዘጋጀው ፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 69 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ነገር ግን ቀኑ በዓል፣ እሁድ ቅዳሜ ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።

10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ካለም ፓራፍ መደረግ አለበት።

11. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል ፈጽሞ እቃውን በሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል/ይኖርባታል/።

12. በጨረታ ያላሸነፉ ተጫራቾች አሸናፊው ውል ከፈጸመ በኋላ የጨረታው ማስከበሪያ የሚመለስ ይሆናል ።

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 0116220730/0116220609 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን የሞላሌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-12 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ሞላሌ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Jul 28, 2026)
  • Posted at: 2026-07-28T08:26:16.000Z
← Back to all tenders