Freight and cargo transport
የምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል የመኪና የጭነት ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለ2019 በጀት አመት ተኝተው ለሚታከሙ ታካሚዎች አገልግሎት የሚዉል የመኪና የጭነት ኪራይ ባሕር ዳር ደርሶ መልስ ኦክስጅን ሲሊንደር አስሞልቶ ጭኖ ለማምጣት እና መዳህኒት ከጎንደር ወደ መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለማጓጓዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የመኪናውን ሊቭሪ (የባለቤትነት ማረጋገጫ) ፎቶ ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ለጨረታ የሚቀርበው ተሸከርካሪ ለደረቅ ጭነት አገልግሎት የሚውል መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በጨረታው የሚያሸንፈው አካል ኦክስጅን ሲሊንደር ያልተሞላውን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ጭኖ ባሕር ዳር ኦክስጅን ማምረቻ አስሞልቶ መተማ ሆስፒታል ማምጣት አለበት፡፡
- የመድን ኢንሹራንስ ውል ያላቸው እና ኮፒውን ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት በምእራብ ጎንደር ዞን መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም መግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታውን ከሐምሌ 20/2018 እስከ ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም ነሐሴ 06/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ የሌለው እና በሰነዱ ላይ ስም እና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጭነት ዋጋ አንድ በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማሰያዝ አለባቸው ወይም በጥሬው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- የጭነቱ አይነት በቢያጆ ሲሆን ምዕ/ጎ/ዞን ፍትህ መምሪያ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት መ/ቤቱ እንዲጫን በሚጠየቅበት ሰዓት በአስቸኳይ ማምጣት የሚችል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 01 74 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- ኦክስጅን ሲሊንደር ከመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ባሕር ዳር ጭኖ አስሞልቶ ለማምጣት በሚሄድበት ቀን በመብራት መጥፋት ወይም በወረፋ ምክንያት ቢዘገይ ወረፋውን ጠብቆ አስሞልቶ መምጣት ግድ ነው፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-12 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Metema General Hospital
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T06:14:40.000Z