Industrial machinery and installation
በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ፣ ለሁለተኛ እና ለሶሰተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ
በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.
- ሎት1.የሰብል ሙቀት መለኪያ (Mositure Meter) ለሶሰተኛ ጊዜ፣
- ሎት2.የቤት ማስዋቢያ የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ
- ሎት3.የመኪና መላዋዋጫ ዕቃዎች ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ፣
- ሎት 4. የኮምፒውተር ዕቃዎች ለሁለተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራቲ (ዋስትና) ወይም ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው።
- ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለበት። እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና ሲፒኦ ሲያሲይዝ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት። ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ።
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለበት።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ 350 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለሁለተኛ እና ለሶሰተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሰራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን በ10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው፤ በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል። ለሁለተኛ እና ለሶሰተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- ቅዳሜ ዩኒየኑ የስራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
- የጨረታው አሸናፊ በጨረታው ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት።
- የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ (መርጦ) መሙላት አይቻልም፣ አሽናፊው የሚለየው በተናጠል ይሆናል የሎት2 አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል። አሽናፊው የአሸነፈውን እቃ በፍትህ ውል ከተመረመረ ወይም ከተመዘገበ የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል።
- አሸናፊው ያሸነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ያቀርባል። ለሰራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውም ወጭ አሸናፊው ይሸፍናል። የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል።
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስ/ቁ 09 11 59 05 34/ 058 320 1670 መጠየቅ ይቻላል ።
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.
Tender details
- Deadline: 2026-08-06
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 8፡00
- Bid opening: 2026-08-06 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 8፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Merekeb Farmers' Cooperative Union
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 350 ብር
- Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T06:33:56.000Z