Disposal, scrap and surplus sales

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተ የ2018 ዓ/ም የተመረተ በቆሎ ለምግብ /ለዘር/ አገልግሎት የሚውል እና ለምግብ የሚውል የተፈለፈለ ሩዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃ.የተ የ2018 ዓ/ም የተመረተ በቆሎ ለምግብ /ለዘር/ አገልግሎት የሚውል እና ለምግብ የሚውል የተፈለፈለ ሩዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም ለመወዳደርመስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በሥራ ዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና (ቲን) ያላቸው።
  2. የግዥው መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ አሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ (በሲፒኦ) ከታወቀ ባንክ በጥሬው ማስያዝ የሚችሉ።
  4. ጨረታው ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ለእያንዳንዱ የሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፍል ጉና የዘር ብዜትና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን በሚገኝበት ደብረ ታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ደሴት ላይ ቡና ባንክ ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ወይም በተወካዩ ሰው መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የሰብል አይነት በቆሎ BH546 ብዛት = 8822.97 ኩንታል እና በቆሎ BH661 ብዛት = 3251 በድምሩ 12073.97 እና ለምግብ የሚውል የተፈለፈለ ሩዝ ብዛት = 101.27 ኩንታል ነው።
  7. መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶች በጥንቃቄ በፖስታ ታሽጎ ጉና ዘር ብዜትና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን በሚገኝበት ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ደሴት ላይ ከሚገኘው ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
  8. ለዘር አገልግሎት ለሚፈልጉ ሙሉ በማሳ ላይ ያለውን የጥራት ክትትል መረጃ ይሰጣል።
  9. ጨረታው የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል።
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ (ታሽጎ) በዚሁ ቀን 4፡30 ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይዛወራል።
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ (ኢቨሎፕ) በጥንቃቄ በማሸግ የድርጅቱን ክብ ማህተም በመምታት በዩኒየኑ ግዥና ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ።
  12. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሌሎች ያልተካተቱ ሁኔታዎች ካሉ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃል።
  13. የሚሸጠው በቆሎ መጠኑ (ኩንታሉ) ብዛት = 12073.97 እና ሩዝ መጠን (ኩንታሉ) = 101.27 ነው።
  14. ዩኒየኑ አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ውጤት ነው። ይህም የዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሰረት የሚፈፀም ይሆናል።
  15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 30 70 99 26 / 09 26 13 56 /09 18 21 87 40 / 09 18 01 85 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

ጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-08-07 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T06:37:31.000Z
← Back to all tenders