Computers, laptops and workstations

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ (ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ብዛት 5፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር ብዛት 20፣ እና ፕሪንተር ብዛት 02 በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በማወዳደር በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤና እና በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው። ማህበሩ ለብቁ ወጣቶች እና PEHP ፕሮግራም ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ (ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ብዛት 5፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተር ብዛት 20፣ እና ፕሪንተር ብዛት 02 በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በማወዳደር በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላ ላችሁ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ባህር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ያለምንም ስርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት አንድ ወጥ በሆነ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው።
  7. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ስዓት ላይ ይታሸጋል። በእለቱ በ9፡00 ስዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል።
  8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9.  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 7360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የአማራ ልማት ማህበር
ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-06
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Bid opening: 2026-08-06 15:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Development Association (ADA)
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T06:54:35.000Z
← Back to all tenders