Fuel, lubricants and solid fuel

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የመኪና እና የጀኔሬተር ቅባትና ዘይት፣ የተሽከርካሪ መድን ሽፋን ኢንሹራንስ እና ህትመት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2019 በጀት አመት

  • 1ኛ. የመኪና እና የጀኔሬተር ቅባትና ዘይት፣
  • 2ኛ. የተሽከርካሪ መድን ሽፋን ኢንሹራንስ
  • 3ኛ. ህትመት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላ ላችሁ።

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይቻላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ እና ንብረት አስተዳዳር ቡድን በቢሮው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኢንቨሎፕ አሽገው ከሐምሌ 20/2018 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 04/2018 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ነሐሴ 05/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል። ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡

9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ጠ/ፍ/ቤት ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 02 56 65 / 09 08 64 99 67 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid opening: 2026-08-11 09:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Supreme Court
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T07:03:16.000Z
← Back to all tenders