Vehicle rental

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የአይሱዚ የመኪና ኪራይ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማስጫን ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቅ ጎጃም ዞን በባሶ ሊበን ወረዳ የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የአይሱዚ የመኪና ኪራይ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለማስጫን ይፈልጋል።

ሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፍቃዳቸውን ያሳደሱ።
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግዥ መጠኑ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር እና በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚያሳትፍ፣ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የተመዘገቡና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ በማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየጁቤ የመ/ደ/ሆስፒታል የግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 ብር 200 (ሁለት መቶ) ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
  7. የጨረታ ሰነዱን በአንድ ፖስታ በማሸግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለባሶ ሊበን ወረዳ የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ በ16ኛ ቀን ከጥዋቱ 3፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት ከጥዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 በግልጽ ይከፈታል የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የማያግድ መሆኑን እንገልፃለን።
  10. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም አለበት። በተገለፀው የግዜ ገደብ ያልቀረበ እና ውል ያልፈፀመ እንደሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ መ/ቤቱ ውርስ ያደርጋል።
  11. ውድድሩ በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ የሚለይ በመሆኑ ተጫራቾች ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል።
  12. አሸናፊው ድርጅት እስከ ሰኔ 30/2019 ዓ.ም ድረስ ለመጫን ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት።
  13. ተጫራቾች ዋጋ መሞያው ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ስርዝ ድልዝ ካለም ፓራፍ መደረግ አለበት።
  14. ሆስፒታሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  15. የጨረታ ዝርዝሩ የጨረታ ማስታወቂያው ጋር ተያይዟል።
  16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 246 0274 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን 3፡30
  • Bid opening: 2026-08-11 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን 4፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የየጁቤ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
  • Bid bond: 3,000 (ሶስት ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Jul 27, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T07:07:22.000Z
← Back to all tenders