Disposal, scrap and surplus sales

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሐራጅ ጨረታ ቁጥር 04/2018/19 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ማሳሰቢያ፦ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን;

በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ ዕሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖሩም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡

3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ሙሉ ቀን በሥራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል፡፡

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እና የሚያበቃበት እንዲሁም ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-

.

የእቃው አይነት

የጨረታው

አይነት

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

ጨረታው የሚጀምርበት ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

ስልክ ቁጥር

 

1

ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች

ሐራጅ

 

22/11/2018

 

27/11/2018

 

4:00

 

8:00

 

0221118429

/0222118925

 5. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡

6. በሐራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆን ማለትም፤

  • ለምድብ 01, ተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 331,200.00፣
  • ለምድብ 02, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 28,000.00፣
  • ለምድብ 03, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 193,700.00፣
  • ለምድብ 04,ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 768,400.00፣
  • ለምድብ 05, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 539,000.00፣
  • ለምድብ 06,ተሽከርካሪመለዋወጫዎች ብር1,406,400.00
  •  ለምድብ 07, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 934,000.00፣
  • ለምድብ 08, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 781,500.00፣
  • ለምድብ 9, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 129,400.00፣
  • ለምድብ 10, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 186,500.00፣
  • ለምድብ 11, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 684,000.00፣
  • ለምድብ 12, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 102,700.00፣
  • ለምድብ 13, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 618,700.00፣
  • ለምድብ 14,ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 109,500.00፣
  • ለምድብ 15, ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ብር 26,100.00

(Customs Commission Adama Branch) ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሠራት ያሠሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡

7. በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡትን እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ስድስተኛው ቀን ከ4፡00 ሰዓት ጀምሮ ኦንላይን ላይ ለየምድቦቹ በተሰጠው ሰዓት መሠረት መጫረት ይቻላል፡፡

8. በሐራጅ ጨረታ የእቃዎቹ የመነሻ ዋጋ ያልተወሰነላቸው ስለሆነ የመነሻ ዋጋ በተጫራች የሚሰጥ ይሆናል ፡፡

9. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን ፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሦስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡

11. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡

12. ከላይ በተ/ቁ 10 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሠሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን፡

NB:- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎች ያላሟሉ ተጫራቾች ቢያሸንፉ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዙት ሲፒኦ ለመንግሥት ገቢ የሚደረግ እና እቃው በድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/ 011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- አዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ ቁጥሮች 022111እና 0222118925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-03 14:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T08:56:35.000Z
← Back to all tenders