Seeds, seedlings and planting material

ናቡ ኢትዮጵያ የአቮካዶ ችግኝ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የአቮካዶ ችግኝ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ናቡ ኢትዮጵያ (The Nature and Biodiversity Conservation Union (NABU) ETHOPIA፣ ደቡብ ምዕራብ ሪጅናል ጽ/ቤት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን በሚገኙ ሦስት ወረዳዎች (ጨታ፣ ጊምቦ እና ገዋታ) እየተገበረ ላለው “Strategic Partnership Agreement" ፕሮጀክት ለሚደገፉ ተጠቃሚዎች የሚሰራጭ እስከ 2000 /ሁለት ሺህ/ የሚሆን የተዳቀለ /grafted Avocado seedings/ ከህጋዊ አምራቾች /አቅራቢዎች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

በዚህም መሰረት ከታች የተቀመጠውን ዝርዝር መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ አምራቾች/ አቅራቢዎች/ የችግኝ መግስጫ (Seeding's Specification) ላይ በተቀመጠዉ መሰረት ቫትን ጨምሮ የአንዱን ችግኝ መሸጫ ዋጋ

1. ያለትራንስፖርት እና

2. እስከ ካፋ ዞን ጨታ ወረዳ ኮላና ቀይ ቀበሌዎች (በአንድ መስመር) ከቦንጋ ከተማ 65ኪ/ሜ ፡ ጊምቦ ወረዳ ተጋ ቀበሌ ከቦንጋ ከተማ 40 ኪ/ሜ ድረስ ያለውን የማጓጓዣ ዋጋን ጨምሮ በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (Profomma) ሞልታችሁና በኤንቬሎፕ አሽጋችሁ ቦንጋ ከተማ ብሔራዊ ቡና ሙዚዬም ከፍ ብሎ በሚገኘው የናቡ ኢትዮጵያ ደ/ም/ማ/ጽ/ቤት ወይንም በፈጣን SMS በቢሯችን ፖ.ሳ.ቁ 130 ቦንጋ ብላችሁ ከቀን 22/11/2018ዓ.ም እስከ 28/11/2018ዓ.ም በሥራ ሰዓት ዉስጥ እንድታስገቡ እያሳሰብን ጨረታዉ በቀን 29/11/2018ዓ.ም በ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቦንጋ ከተማ በሚገኘው የናቡ ኢትዮጵያ ደ/ም/ማ/ጽ/ቤት የሚከፈት መሆኑንን እንገልጻለን::

በጨረታው ለመወዳደር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. ለ 2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለዉ፣

2. የዘመኑን ግብር የከፈለ፣

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ተመዝጋቢ የሆነ፣

4. ለሚከፈለው ገንዘን ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት የሚችል

5. ከላይ የተጠቀሱትን ህጋዊ ሰነዶች ኮፒ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣

ማሳሰቢያ፡

  • የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ከ ሐምሌ 22-28/2018ዓ.ም ባሉት አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ስለሆነ በ ፖስታ ሳጥን ቁጥር የምትልኩ ተጫራቾች በፈጣን SMS በኩል መላክ ይጠበቅባቸዋል::
  •  የአንዱን ችግኝ ዋጋ ያለ ትራንስፖርት እና ከላይ እስከተጠቀሰው አደራሻ ድረስ ማድረሻ ትራንስፖርት ዋጋን ጨምሮ በሚል በሁለት መንገድ ዋጋ በማቅረብ ሞልታችሁ ማስገባት ይጠበቅባችኋል::
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

2. የሚገዛው የአቮካዶ ችግኝ መገስጫ (Seedling's Specification)

  • Grafted Hass
  • Grafted Ettinger

3. ለበለጠ መረጃ የፕሮጀክት ባለሙያ አቶ ልሳኑ ተሾመን በስልክ ቁፕር +251910506379 ማግኘት ይቻላል::


Tender details

  • Deadline: 2026-08-04
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid opening: 2026-08-05 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nature and Biodiversity Conservation Union (NABU)
  • Published on: Reporter (Jul 29, 2026)
  • Posted at: 2026-07-29T14:36:30.000Z
← Back to all tenders