Vehicle purchase

ኢትዮጵያ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ /መኢኢግ/ ሃይብሪድ ተሽከርካሪ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡ መኢኢግ/ግጨተሽ 05/2018

1. የግዥ ፈፃሚው ስም መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ

2. የግዥው ዓይነት: ሎት አንድ ፡ ሃይብሪድ ተሽከርካሪ ግዥ

3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡

የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ፣የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN Number) እና አቅራቢነት ኦን-ላይን የተመዘገበና የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።

4. የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ፡ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 102 እና 105 ሀይሌ ጋርመንት የቀድሞ ሪቬራ ሆቴልማግኘት ይችላሉ።

5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን፡ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በእያንዳንዱ በሚወዳደሩበት ሎት ላይ ለተጠቀሰው ጠቅላላ ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተወሰነ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Performance bond) ተጫራቹ ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% (10 ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሲያቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያው ይለቀቅለታል።

7. የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የሚከፈል የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በገንዘብ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይቻላል።

8. የመወዳደሪያው ሰነድ የሚቀርበውፋይናንሻል ሰነድኦርጅናል፣ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ እና ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ የቅጂ ብዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ አንዳንድ ኮፒ ሆኖ ሰነዶቹ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸውና የድርጅቱ ማህተም ያለባቸው መሆን አለባቸው፤ እንዲሁም ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዕቃዎች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል መግለጫ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በግልፅ ከላይ በሚታይ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ብለው ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።

10. ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ፡- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡30 የስራ መውጫ ባሉት ሰዓቶች ሲሆን ጨረታው የሚዘጋው በቀን 08 ነሀሴ 2018 ከጠዋት 4፡20 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ነሀሴ ቀን 08/ 2018 ከጠዋት 4፡30 ይከፈታል።

11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተቀመጠውን ስፔስፊኬሽንም ሆነ የዕቃ ዓይነት ከሌለው የለንም ወይም ሰረዝ (~) ማድረግ እንጂ በአማራጭ መሙላት አይችልም።

12. ግሩፑ በጨረታ ሰነዱ በሎት አንድ ላይ የተቀመጠውን የተሽከርካሪ ዝርዝር ፍላጎት በተጨማሪ በምስል ማቅረብ ይችላል።

13. ግሩፑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  • ተጨማሪ መረጃ ሲፈልጉ፡_
  • ስልክ ቁጥር፡- 0967 26 16 36/0996117472 ሀይሌ ጋርመንት የቀዶ ሪቬራ ሆቴል አዲስ አበባ፣

ኢትዮጵያ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ /መኢኢግ/ 


Tender details

  • Deadline: 2026-08-14
  • Bid closing time: 10:20
  • Bid opening: 2026-08-14 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ/መኢኢግ/
  • Bid bond: 2% በእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
  • Posted at: 2026-07-30T08:08:09.000Z
← Back to all tenders