Oromia

በአርሲ ዞን የመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችና የቀበሌ አስተዳደሮች አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁ_01/2019

በአርሲ ዞን የመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችና የቀበሌ አስተዳደሮች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1. ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ሎት 2. የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 3. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 4. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 5. ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1.ለተጠየቁት የግዥ ዕቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer Registration No)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በፌዴራል፤ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዥዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ለጽህፈት መሳሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ)፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፤ ለጽዳት እቃዎች እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ) በመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000075175648 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ ንብረት አስተዳደር ማስወገድና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ ቅፅር ግቢ በተዘጋጀው ቦታ ፖስታው ይከፈታል።

5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ለጽህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ብር 40000.00 (አርባ ሺህ)፣ ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20000.00 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም ለጽዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000.00 (አስር ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና ዕቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አቦምሳ ከተማ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።

7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 09 22 07 37 69, 09 13 39 57 62, ይጠይቁ።

በአርሲ ዞን የመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-08-17 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን 4፡30 ሠዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Merti Wereda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
  • Posted at: 2026-07-30T08:40:02.000Z
← Back to all tenders