Disposal, scrap and surplus sales
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ እስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የግልፅ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ
- የተለያዩ አልባሳት፣
- ኮንስትራክሽን፣
- ኤሌክትሮኒክስ፣
- የቤት እቃ፣
- የቤት ማስዋቢያ፣
- ጫማዎች፣
- ምግብ ነክ፣
- እስፔርፓርት
- የጽዳት እቃ እና
- ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች በ28/11/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።
ስስሆነም በጨረታው ላይ ስመካፈል የምትልጉ ተጫራቾች፡-
- ለግልፅ እና ለሐራጅ ጨረታ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ።
- ለሐራጅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማቅረብ የሚችል።
- ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማቅረብ የሚችል።
- ለሐራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል።
- ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በዐ5 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት።
- እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በዐ5 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
- ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
- ተጫራቾች የሞሉትን የግልፅ ጨረታ ሰነድ ከቀን 28/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በ30/11/2018 ዓ.ም 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው በ30/11/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡15 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
NB: አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-06
- Bid closing time: 10:15
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-08-06 10:15
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Somali
- Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
- Posted at: 2026-07-30T09:04:07.000Z