Disposal, scrap and surplus sales
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የፕላስቲክ ምርቶች መካከል Common Plastic Sheet መሸጥ ይፈልጋል
Description
የምርት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-APE/01/2019/Local
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከሚያመርታቸው የፕላስቲክ ምርቶች መካከል Common Plastic Sheet የተባለውን ምርት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከነሐሴ 01/2018 እስከ ጥቅም 30/2019 ዓ.ም ድረስ መሸጥ ይፈልጋል።
ምርቱ መልኩ ቢጫ (Yellow) ሲሆን ውፍረቱ በአማካይ 0.175ሚሜ ወርዱ ደግሞ 8.08 ሜትር ነው። ለሽያጭ የቀረበው ጠቅላላ ምርት ብዛት 1,358,626 ካሬ ሜትር ሲሆን ምርቱ በጥቅል የሚቀርብ ሆኖ የአንዱ ጥቅል ርዝመት በአማካይ 130 ሜትር ወርድ 8.08 ሜትር ነው። የምርቱ የአንድ ካሬ ሜትር መነሻ የጨረታ ዋጋ ከነቫቱ ብር 10.40 ነው።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ቅጅ (Copy) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋው ብር 1,000,000.00 የሆነ CPO በፋብሪካው 9 ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የሕጋዊነት ሠነዶቻቸውን ቅጅ (Copy)፣ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችን ማስረጃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 206 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
- 10ኛው ቀን ሕዝባዊ በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- በውድድሩ ለአንድ ካሬ ሜትር ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል።
- አሸናፊው ምርቱን ለማንሳት በቅድሚያ ብር 2,000,000.00 ዋጋ ያለው የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ(CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ዘገባ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፋብሪካው ስም በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ በማቅረብ አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት እለት ጀምሮ ባሉት በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።
- በየወሩ ማለትም በነሐሴ፣ በመስከረም እና በጥቅምት ወራት የሚነሳው የምርት መጠን እንደቅድም ተከተሉ 500,000 ካ.ሜ፣ 429,313 ኪ.ሜ፣ 429,313 ካ.ሜ ነው። ስለሆነም የውድድሩ አሸናፊዎች ምርቱን ለማንሳት በቅድሚያ በየወሩ የሚያነሱትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ 50% ውል በተያዘ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
- ፋብሪካው ማንኛውንም ዓይነት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ 09-35-98-37-29/ 09 00 90 92 50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-08
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-08 14:30
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Pipe Factory PLC
- Buyer TIN: 0006196550
- Bid bond: 1,000,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 30, 2026)
- Posted at: 2026-07-30T09:37:27.000Z
- Buyer website: https://amharapipe.et/