Vehicle purchase

ኦቢኤም ኮንስትራሽን ድርጅት ለሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ ብዛት 2 (ሁለት) አዲስ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ (Fully Electric EV) ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EV) ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ EV-TENDER PSM001/2018

መሥሪያ ቤታችን ለሠራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት የሚውሉ ብዛት 2 (ሁለት) አዲስ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ (Fully Electric EV) ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ህጋዊ መስፈርቶች

  • በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
  • ወቅታዊ የመንግሥት ግብር የከፈሉበትን ማረጋገጫ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችሉ፤
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር (Suppliers List) የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የዕቃው ዓይነት እና ብዛት በአጭሩ

  • የዕቃው ዓይነት፡ ለሠራተኞች ሰርቪስ የሚሆን ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠራ (EV) ሚኒባስ
  • ብዛት፡ 2 (ሁለት) 00 ኪሎ ሜትር (Zer Kilometer)
  • የመጫን አቅሙ፦ ከ4-16 ሰው (4-16 person)

3. የጨረታ ሰነድ አቀራረብ እና መመሪያ

  • ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢፍቱ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ኦቢኤም ኮንስትራክሽን ድርጅት - ፋይናንስ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር ሁለት ፐርሰንት (2%) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የቴከኒክ እና የፋይናንሻል ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በማድረግ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ወስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  • ጨረታው በ8/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ላይ ተዘግቶ፣ በ9/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅታችን የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ይከፈታል።
  • መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኦቢኤም ኮንስትራሽን ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-14
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid opening: 2026-08-15 10:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: OBM Construction S.C.
  • Buyer address: ሜክሲኮ ኮሜርስ ፊት ለፊት በሚገኘው የኦ.ቢ.ኤም ኮንስትራክሽን አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ቢፍቱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
  • Posted at: 2026-07-31T07:28:55.000Z
← Back to all tenders