Shares, securities and other sales
የአክሲዮን ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት እነ አወጣኸኝ ኪሮስ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሰይፈ አምባዬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/301770 በ23/05/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/335483 በ7/8/2017ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/335483 በ23/03/2018ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአኪር ኮንስትራክሽን ኃ /የተ/የግ/ማህበር ውስጥ ኛ እና 2ኛ የፍ/ባለዕዳ ያላቸው አክሲዮን የማህበሩ ጠቅላላ አክሲዮን ብዛት 20,000(ሃያ ሺህ) የአንድ አክሲዮን ዋጋ 1000( አንድ ሺህ) ሲሆን በኛ የፍ ባለዕዳ አቶ ሰይፉ አምባዬ ፋንታ የአክሲዮን ብዛት 16,ooo( አስራ ስድስት ሺህ) አጠቃላይ የአክሲዮን ዋጋ 16,000,000( አስራ ስድስት ሚሊዮን)ብር 2ኛ የፍ/ባለዕዳ አቶ ይኩኖ አምላክ አምባየ የአክሲዮን ብዛት 4000( አራት ሺህ) አጠቃላይ አክሲዮን ዋጋ (አራት ሚሊዮን)ብር የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 20,000,000 ( ሃያ ሚሊዮን ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 27 ቀን 2018ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-09-02 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
- Posted at: 2026-07-31T07:30:34.000Z