Oromia
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣ የጽዳት እቃዎችን፣ የደንብ ልብሶችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎችን እና የተሽከርካሪ መኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የደንብ ልብሶች
- ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች
- ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 4 የተሽከርካሪ መኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች
- ሎት 5 ቋሚ የቢሮ እቃዎች
በመሆኑም ተጫራቾች፦
1) በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት፣የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ እና ለ 6 ወር ብቻ የሚያገለግል በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2) ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 6,000 (ስድስት ሺህ ብር) ብቻ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል።
3) ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል በሪጅን ጽ/ቤቱ 7ኛ ህንጻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4) ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሰረት ብቻ መሆን ይኖርበታል።
5) ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6) ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚያው እለት 8፡30 ይከፈታል። 11ኛው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀንየሚከፈት ይሆናል።
7) ጽህፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን ዕቃዎች ጽ/ቤቱ ግምጃ ቤት 7ኛ ፎቅ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
አድራሻ፡- ጅማ ከተማ አባ ጅፋር አደባባይ የጅማ ከተማ መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ ዋስትና ህንጻ
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ፦ 09 17 28 36 17 ወይም 09 17 87 80 57 መደወል ይቻላል።
ት/ ቤት ጅማ
የመንግስት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር
ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-12
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 8፡00
- Bid opening: 2026-08-12 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 8፡30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Government Employees Social Security agency South West Ethiopia Region Bureau
- Buyer address: ጅማ ሙዚየም አጠገብ
- Bid bond: 6000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
- Posted at: 2026-07-31T08:00:29.000Z