Well drilling and boreholes

ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለማሰራት ስራ የተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

300 ሜትር ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ

የጨረታ ማስታወቂያ

1. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ለማሰራት ስራ የተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

2. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈታድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግሰት የአቅራቢዎች የአገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።

3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ላፍቶ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን ለመጠጥ የሚውል ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ በሚመለከት የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ፖስታ ኦሪጂናል እና ኮፒ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) ለ90 (ዘጠና) ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ከፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ በላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተከርስቲያን ስም የተዘጋጀ ማቅረብ አለባቸው።

6. ጨረታው ነሀሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሀሴ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ላፍቶ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ቢሮ ይከፈታል።

7. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0948 818 283 / 0911 245 219 መደወል ይችላሉ።

ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-10
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-10 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lafto Debre Teghuan Saint Michael Church
  • Bid bond: 20,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Jul 31, 2026)
  • Posted at: 2026-07-31T08:10:11.000Z
← Back to all tenders